Thursday, May 26, 2016

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ ብርሃነ ኪዳነማርያም ከስልጣኑ ተባረረ

timthumb

(-ሐበሻ) የሕወሃት ዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ከአቶ ስብሃት ነጋ ጋር የቅርብ የቢዝነስ አጋር የነበረው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮሮፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አይተ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም ከስልጣኑ መባረሩ ተሰማ:: በዚህ ሳምንት ሌላው የሕወሓት አባልና የድህንነት / ምክትል አቶ ኢሳያስ መባበሩም አይዘነጋም::
በሃገረ ኤርትራ የተወለደውና የሕወሓት ታማኝ ሰዎች ማከከል አንዱ በመሆኑ ሕወሃት የሚያስተዳድረው ኤፈርት ዳይሬክተርም ነበር:: የቀድሞው የህወሃት ፕርፓጋንዳ መፈልፈያ ዋልታ ኢንፎርማሽን ማዕከልም ዋና ሰው ሆኖ ያገለግል የነበረው አቶ ብርሃነ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲና የወጋገን ባንክ የቦርድ አባል ነበር::
አቶ ብርሃነ የኢፈርት ዳይሬክተርነትን ሥራ ከወ/ አዜብ ተረክቦ ይሰራ እንደነበር አይዘነጋም::
አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከስልጣናቸው መባረር እንዲሁም ከጥቂት ቀናት በፊት የድህነቱ ምክትል ሰው አቶ ኢሳያስ መሰናበት በኋላ ወይዘሮ አዜብ ከነልጃቸው አሜሪካ መግባታቸው አነጋጋሪ ሆኗል::

Zehabesh

No comments: