Sunday, May 22, 2016

ኦሮሞዉን ከአማራ ለማገጨት አዲስ ፕላን ተነድፏል!!



በልኡል አለም
የብዙሀን ኢትዮጵያዊያን የኦሮሞ ወገኖቻችን ሞትና እስር እንዲሁም የአካል ጉዳት መንስኤ የሆነዉ የኦሮሚያ ማስተር ፕላን በተለየና በተቀናበረ መልኩ ሊተገብር መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል። ከ5 ቀናት በፊት ጌታቸዉ የተባለዉ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ባልደረባና የህዝብ ጠላት ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት ላይ በጀርባ በዚሁ በኦሮሚያ ማስተር ፕላን ዙሪያ አዲስ የትግበራ ዘዴ ላይ ከፍተኛ ዉይይት ተደርጓል።

Ethiopia: Make Peaceful Change Impossible? Make Violent Revolution Inevitable!በመጀምሪያ በመላዉ ሐገሪቷ ላይ የአረንጓዴ ልማት እና የከተማ እድገት መርሐ ግብር እንዲሁም ከማስተር ፕላን ዉጭ የተሰሩ ህገ ወጥ ግንባታዎችን በማፍረስ ተጠንስሶ ዋናዉ አላማዉ የሆነዉ መሬት መቀራመቱ ንድፍ ተዋቅሮለት የድርጊት ሙከራዎች እየተከወኑ ይገኛሉ።

በዋናነት ይቅርታን የጠየቀና አመጽ የተቀሰቀሰባቸዉን የኦሮሚያ ስፍራዎች ለመካስ በሚመስል መልኩ የተቀየሰዉ የዝርፊያ እና ኦሮሞዉን ከአማራዉ ጋር የማገጨት አዲስ የተንኮል መርሐ ግብር በወያኔ ባለስልጣናት በተለይም አባይ ጸሐዬ፣ አባ ዱላ ገመዳ፣ በረከት ስሞን እንዲሁም በፖሊስ ኮሚሽን ባለስልጣናትና የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ጋር በአንድነት ያበረ ድብቅ አጀንዳ የሚተገበር የቡድን ግፍ ነዉ።

በመሆኑም በመላዉ ሐገሪቷ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የዉድ ሐገራችንን ጭቁን ገበሬ በማፈናቀል መሬቱን በግፍ ለመቀማት የተጠነሰሰዉን ሴራ ለማክሸፍ ዘር ሐይማኖት ጎሳ ባለመለየት በአንድንት እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Ecadeforum

No comments: