Monday, May 23, 2016

ፌስቡክ ላይ በጻፈው ጽሁፍ ምክንያት የሽብር ክስ የቀረበበት ዮናታን ተስፋዬ በነጻ እንዲሰናበት ጠይቋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በመቃወም በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ሰበብ ለእስር ተዳርጎ የሽብር ክስ የቀረበበት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሰብዓዊ መብት አራማጅ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከቀረበበት ክስ በነጻ እንዲሰናበት በክስ መቃወሚያው ላይ ጠይቋል፡፡
ድረ ገጽን በተለይ በግሉ የሚጠቀምበትን የፌስቡክ አካውንት በመጠቀምበኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን አመጽና ብጥብጥ እንዲቀጥል ቀስቅሷልበሚል የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ያቀረበበት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ግንቦት 15/2008 . ከፍተኛው /ቤት ልደታ ምድብ 19 ወንጀል ችሎት ቀርቦ የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ አቅርቧል፡፡ ዮናታን ስድስት ነጥቦች ባሉት የክስ መቃወሚያው ከተመሰረተበት የሽብር ክስ በነጻ እንዲሰናበት አመልክቷል፡፡
ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ የተመለከተው ‹‹….አመጽና ብጥብጥ ለማስቀጠልና ለማነሳሳት በፌስቡክ ድረ ገጽ ቀስቃሽ ጽሁፎችን መጻፍ ድርጊት›› በተከሳሹ ላይ ከተጠቀሰው የጸረ ሽብርተንነት አዋጅ አንቀጽ 4 ጋር የተቀራረበ አለመሆኑን የወ//ሕግ///.112 ጠቅሶ፣ ከድንጋጌው ውጭ የቀረበና ‹‹የሽብርተኝነት ተግባር›› ባለመሆኑ የቀረበው ክስ ተሰርዞ በነጻ እንዲሰናበት /ቤቱን ጠይቋል፡፡
አቶ ዮናታን የቀረበበትን ድርጊት ወንጀል (ሽብርተኝነት) የሚያደርገው የህጉ ልዩ ክፍል የአዋጁ አንቀጽ 3 መግቢያ የሀሳብ ክፍል ስለአለመሟላቱና በክሱ ተመልክቶ ስለመቅረቡ በመጥቀስ ድርጊቱ በአዋጁ የማሸፈንና ወንጀልም ባለመሆኑ ክሱ ተሰርዞ በነጻ እንዲሰናበት አምልክቷል፡፡ 
በተጨማሪም ተከሳሹ የቀረበበትአመጽና ብጥብጥ… ‹‹….የመልካም አስተዳደር እጦት ችግር….›› እንጂ የኦ.. ተግባር ያለመሆኑ የህግ ግምት ሊወሰድበት የሚገባ መሆኑንንም በክስ መቃወሚያው ላይ ገልጹዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ተከሳሹ ጽፎታል ተብሎ በማስረጃነት የቀረበው ጽሁፍና ፈጽሞታል ተብሎ የቀረበበት ድርጊት የወንጀል ኃላፊነትን የማያስከትልና ህገ-መንግስታዊ ጥበቃ የተደረገለት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መሆኑን በማስታወስ ክሱ እንዲሰረዝና በነጻ እንዲሰናበት ጠይቋል፡፡
ተከሳሹ የቀረበበት ክስ ግልጽ ያለመሆኑንና የቀረበበትን የማስረጃ ዝርዝር በተመለከተም ዝርዝር መቃወሚያውን ለፍርድ ቤቱ አስገብቷል፡፡ ከሳሽ አቃቤ ህግ በተከሳሽ የቀረበው የክስ መቃወሚያ ላይ መልስ እንዲሰጥበት ለመጠባበቅ /ቤቱ ለግንቦት 25/2008 . ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዛሬው የችሎት ውሎ 19 ወንጀል ችሎት ሙሉ ለሙሉ በተከሳሾች በመሞላቱ አንድም የተከሳሽ ቤተሰብ፣ ወዳጅ እንዲሁም ጋዜጠኛ፣ ታዛቢ ችሎቱን መከታተል ሳይችል ቀርቷል፡፡




No comments: