Tuesday, May 10, 2016

በዓለም-የፕሬስ-ቀን-መሪ-ቃል-የቀመረች-ብቸኛዋ-አገር-ጦቢያ

በዓለም የፕሬስ ቀን መሪ ቃል የቀመረች ብቸኛዋ አገር - ጦቢያ!!
ከተጠያቂነት የመሸሽያ አዲሱ ስትራቴጂፈርሙልኝሆኗል
• ‹‹
ብዝሃነት›› በተመለከተ አገራዊ መግባባት ላይ አልተደረሰም
እንኳን ለዓለም አቀፉ የፕሬስ ቀን አደረሳችሁ! ይባል አይባል ግን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ለነገሩ እንኳን ለማርች 8 የሴቶች ቀን አደረሳችሁ እንደማለት እኮ ነው፡፡ ወይም ደግሞ እንኳን ለዓለም የውሃ ቀን አደረሳችሁ ---- ሊሆንም ይችላል፡፡ (የውሃ ቀን የሚባል በዓል አለ እንዴ?!) በነገራችን ላይ በመላው ዓለም የፕሬስ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በቅርቡ የወጡ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡ የፕሬስ አፈናው በርትቷል፡፡ ጋዜጠኞች በጨቋኝ መንግስታት ይታሰራሉ፤ይገደላሉ፤ለስደትም ይዳረጋሉ፡፡ ይሄ ሁሉ እንግዲህ በአይሲስ አንገታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ የተቀሉትን ጋዜጠኞች ሳይጨምር ነው፡፡
የየአገሩ መንግስታት ጋዜጠኞች ላይ እንዲህ አብረው መነሳታቸው ዓለም ወደ አምባገነን ሥርዓት እያመራች መሆኑን መጠቆምያ ፍንጭ እንደይሆን ክፉኛ ያሰጋል፡፡ ያለዚያማ በብዕር ለሚፋለም ጋዜጠኛ፣ እስርና ግድያን ምን አመጣው? ለመጽናኛ ያህል ከጥቂት ወራት በኋላ ስልጣናቸውን የሚለቁት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ ሰሞኑን ከፕሬስ ጋር በነበራቸው የመጨረሻ የእራት ምሽት ላይ ባደረጉት ቀልድና ትረባ የበዛበት ንግግር፤ፕሬሱ ለዲሞክራሲያቸው መጎልበት ላደረገው አስተዋጽኦ ዕውቅና እና አድናቆት ቸረውታል፡፡ (ከሩቅ የተሰማ ቢሆንም የተስፋ ሽልን ያላውሳል!)
በነገራችን ላይ በእኛም አገር ባለፈው ማክሰኞ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ቀን በፓናል ውይይት ተከብሮ ውሏል፡፡ በዓሉ ዓለማቀፍ ቢሆንም፣እኛ ያከበርነው በራሳችን አገር በቀል መሪ ቃል መሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ (አያደርገውም እንዴ?) እናላችሁ ----- የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በውዝግብ እንዳናወጠ የተነገረለት መሪ ቃል፤የሚዲያ ብዝሃነትን ያከበረች ሀገር - ኢትዮጵያየሚል ነው፡፡

No comments: