Saturday, April 25, 2015

ፌዴራል ፖሊስ በጨርቆስ አካባቢ ያሉ በርካታ ወጣቶችን አፍሰ

ፌዴራል ፖሊስ በጨርቆስ አካባቢ ያሉ በርካታ ወጣቶችን አፍሶ በ4 ከባድ መኪናዎች ሞልቶ ወዳልታወቀ ቦታ ወሰደ። ከታፈሱት ውስጥ ብዙዎቹ በሊቢያ የተሰውት ወገኖቻችን ዘመዶችና ጓደኞች ናቸው።

በአዲስ አበባ የጨርቆስ ክፍለ ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ እየተጨናነቀች ነው። ጭንቅንቁን ያበዛው ደግሞ አንድም ሃዘንተኛው በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ አፈሳ ነው። ሰሞኑን መብራት እየጠፋ ፖሊስ ቤት ለቤት እየሄደ ያፈሰው በተለይ የጨርቆስ ልጆችን ነበረ። በዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት ወጣቶች በተለይ ከዚህ ሰፈር ታፍሰው ተወስደዋል። እንደተለመደው አስረው ያሰቃዩዋቸዋል፤ ወይም አሸባሪ(ኢ.ኤም.ኤፍ) በአዲስ አበባ የጨርቆስ ክፍለ ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ እየተጨናነቀች ነው። ጭንቅንቁን ያበዛው ደግሞ አንድም ሃዘንተኛው በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ አፈሳ ነው። ሰሞኑን መብራት እየጠፋ ፖሊስ ቤት ለቤት እየሄደ ያፈሰው በተለይ የጨርቆስ ልጆችን ነበረ። በዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት ወጣቶች በተለይ ከዚህ ሰፈር ታፍሰው ተወስደዋል። እንደተለመደው አስረው ያሰቃዩዋቸዋል፤ ወይም አሸባሪ ተብለው ሊከሰሱ ይችላሉ፤ ከሁሉም የሚከፋው ግን እንደከዚህ ቀደሞቹ ታፍሰው የደረሱበት ከጠፋ ነው። ስለዚህ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ከወዲሁ ጉዳዩን ሊከታተሉት ይገባል።
እነዚህ እና ሌሎች ወጣቶች ከሶስት ቀናት በፊት በተጠራው ሰላማዊ እልፍ ላይ ተገኝተው፤ ፌዴራል ፖሊስን "የውስጥ አንበሳ፤ የውጭ ሬሳ" ሲሉ ነበር። "ጉልበታችሁን የምታሳዩት እኛ ላይ ብቻ ነው" እያሉም ሲተቹ ነበር። ወጣቶቹ ከብሶታቸው ብዛት፤ በታሪክ ብቻ የሚያውቁትን ወይም በነሱ ዘመን ያልነበረውን ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም "አትመጣም መንጌ" እያሉ ሲያዜሙ ነበር። ከምንም በላይ ግን በሰላማዊ እልፉ ላይ፤ "እዛ አይሲስ፣ እዚህ ፖሊስ" ሲሉ የነበረው አባባል እውነት እየሆነ የመጣ ይመስላል። በርግጥም እዛ አይሲ፤ አገር ውስጥ ደግሞ ፖሊስ ወጣቱን እያመሰው ነው።

No comments: