Friday, April 24, 2015

ለነጻነታቸው ዋጋ የሚከፍሉ ሁሉን የሚያወድስ የሁለት ቀናት ማስታወሻ

“ ለነጻነታቸው ዋጋ የሚከፍሉትን እናወድስ”
“እያንዳንዱ እገዛ ዋጋ አለው” ……………………………….. ለነጻነታቸው ዋጋ የሚከፍሉ ሁሉን የሚያወድስ 
የሁለት ቀናት ማስታወሻ

ለውድ የዞን9  ነዋሪያን
ነገ በዚህ ሰአት ግድም ስድስቱ የዞን9 ጦማርያንጓደኞቻችን እና ሌሎች ሶስት ጋዜጠኛ ወዳጆች ከያሉበት እየታሰሩ ነበር፡፡ በሁለት ቀናት ውስጥ ዘጠኝ ወጣቶች የእስር ህይወታቸውበአሰቃቂው ማእከላዊ ምርመራ ጀመሩ ፡፡አመት ያስቆጠረው ይህ እስር ለሶስት ወር ከሚጠጋ አሰቃቂ የማእከላዊ ምርመራ ቆይታ በኋላአይነቱን ቀይሮ በቃሊቲና ቅሊንጦ ቀጠለ ፡፡ በዚህ አንድ አመት ውስጥ ለዋናው የክርክር ሂደት 25 ጊዜ በተጓዳኝ የተጠሩ የእስረኞችንአያያዝ ሂደት የሚመለከቱ ክርክሮች ደግሞ ለ27 ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡  በዚህ ሂደት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዞን9 ጦማርያንን የሚመለከቱ የተለያዬጽሁፎች የእስራቸውን ሁኔታ የሚያሳዬ መረጃዎች  እያንዳንዱን እስርላይ የሚያሳልፉትን ቀን ቆጠራዎች ታትመዋል ተካሂደዋል፡፡ እነዚህ የግለሰብ የቡድን እና የተቋማት ጥረቶች ተደምረው ከእስሩ ከአነድአመትም በኋላ ዞን9 ጦማርያን ጉዳይ ትላንት የሆነ ያህል የሚታወስ ከማህበረሰብ ሚዲያው በእስር የጠፉት ወዳጆቻችንም እዚህ ያሉያህል አንዲታወሱ ሆነዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአለም ደረጃ የኢትዬጲያ ጭቆናን ደረጃ ማሳያ ምልክት እስከመሆን ደርሰዋል፡፡
አንደሃሳባችን ቢሆን ኖሮ ዛሬ እና ነገን  የዞን9 ጦማርያንን እና ያለመታከት ድጋፍ ሲያደርጉ የከረሙ ብዙ ወዳጆቻችንን“እያንዳንዱ ድጋፍ ዋጋ አለው “ በሚል ቃል በጋራ ልናወድሳቸው እቅድ ነበረን ፡፡  በዚህ ሳምንት የተፈጠረው አሰቃቂ አገራዊ ሃዘን እና ብሄራዊ የሃዘን ቀንንበማስመልከትና ሃዘናችንን ለመግለጽ ስንል ግን ቀኑን ለሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ለማሻገር ወደድን ፡፡ በመሆኑም የዞን9 ጦማርያንንየአንድ አመት እስር እና የማይሰለቹ ደጋፌዎቻችንን  አስመልከቶ ለሁለትቀናት የምናደርገው  “ የእያንዳንዱ ድጋፍ ዋጋ አለው፣ ለነጻነታቸውዋጋ የሚከፍሉትን እናወድስ“ የማስታወሻ ቀናት ከሚቀጥለው ሰኞ ሚያዝያ 19 እና ሚያዝያ 20 ለሁለት ቀናት ይካሄዳሉ፡፡ በነዚህሁለት ቀናት የዞን9 ጦማርያን ጋዜጠኞችን እና ሌሎች ብዙዎች ለነጻነት የሚከፍሉትን ዋጋ እናወድሳለን፡፡
ሰኞ እና ማክሰኞ የማስታወሻ ቀናት

-      የዞን 9 ጦማርያን የተያዙበት ቀን ምን ይመስላል? እያንዳንዳቸውታሪካቸውን ያካፍላሉ
-      ፌደራል ወንጀል ምርመራ በተለምዶውማእከላዊ የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ዝርዝር ምን ይመስል ነበር ? የማእከላዊ ቀናቸውን በዝርዝር ያሳዬናል
-      አመታቸው አንዴት አለፈ የእስርመስመር አዘጋጅተናል፡፡
-      እያንዳንዱ የፍርድ ሂደት አንዴትሄደ? የፍርድ ቤት ሪፓርቶቹን እናነባለን፡፡
-      ሴት እስረኞች ውሏቸው ምንይመስላል? ተደጋጋሚው የመብት ጥሰት አቤቱታስ ? የምናጋራቸሁ ይኖራል ፡፡
-      በአመቱ አስገራሚ የነበሩ በመንግሰትስለ ክሱ የተባሉ ነገሮች ይቀርባሉ ፡፡
-      በመጨረሻም አመቱን አስመልክቶ  ወዳጆቻችን ከቅሊንጦና ከቃሊቲ የላኩት መልክት ይኖራል፡፡
በመሆኑም  ለተከበራችሁ የዞን 9 ነዋርያንም ለነጻነታቸው ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ብዙዎችንበጋራ እንድናወድስ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ ማስታወሻ የሚከተሉትን የፕሮፋይል ምስሎች እና የከቨር ምስል በመጠቀም ማስታወሻ ቀናቱንአንድትቀላቀሉ ትለመናላችሁ::

እያንዳንዳችሁ ስለዞን9 የጻፋችሁ፣ ስለዞን9 ያወራችሁ፣ጽሁፎችን የወደዳችሁ ፣ ያጋራችሁ ፣ እስሩን ስመልክቶ የሚመጡ ዜናዎችን የተከታተላችሁ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ይፈቱ ያላቸሁሁሉም እገዛ ዋጋ አለው ፣ በእናንተ ድጋፍ ሁሉም በመልካም መንፈስ እና ጥንካሬ ላይ ሆነው አመቱን ተወጥተውታል፡፡  ገንዘብና ጊዜያችን መስዋእት አድርጋችሁ ድጋፋችሁን ያሳያችሁ የቤተሰባቸውንጫና የተካፈላችሁ በእናንተ እገዛ አመቱ ቀሎላቸዋል፡፡

የሚከፍሉትን ዋጋ እናወድስ

ስለሚያገባን እንጦምራለን

ዞን9 

No comments: