Friday, April 3, 2015

ወገኖቻችን የመን ውስጥ እልቂት አንዣቦባቸዋል።

ኢትዮጵያ የመን ውስጥ በጦር ቀጣና አካባቢ ሆነው ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ ያሉ 20000 ልጆችሽን አውጪ!!!! ለህዝብ ነው የቆምኩት ብሎ መፎከር ያኔ ነው!!!!!!! የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት እነዚህ አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ ኑሮን ለማሻሻል ከተለያዩ የአገሪቱ ገጠራማ ክፍሎች የተሰደዱ መሆናቸውን ገልጿል። ሀገር መምራት ማለት ለህዝብ ፈጥኖ መድረስ ነው~~ ሌላው ትርፍ ነው።
 እኔን የገረመኝ ዜጋውን ከየመን ሳያወጣ ሳውዲአረብያ እና አጋሮችዋ ያደረገችው እርምጃ ልክ ነው ብሎ መግለጫ መስጠቱ ነው ለዚህም ኢትዮጵያውያን በዙ ዋጋ እንደሚከፈሉ ግልፅ ነው ምናለ ቅድሚያ እዛው ላለው ዜጋው ቢያስብ !! ስለሆነም ከፈጣሪ በታች ያለው የዲያስፖራ ወገኖች ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ በማመን እኛም በቻልነው ነገር ሁሉ ወገኖቻችንን ማሰቡ ተገቢ ነው እላለሁ
ወገኖቻችን የመን ውስጥ እልቂት አንዣቦባቸዋል። ምን ማድረግ ይበጀን ይሆን ወንድማችንን አንዳርጋቸውን ለመጥለፍ አይሮፕላን ተላከ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የቦንብ ናዳ ሲወርድባቸው ግን በቴዎድሮስ አድሃኖም አማካይነት የተላከላቸው የስልክ ቁጥሮችን ነው። የመን ለሚገኙ ወገኖቻችን ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ
የወያኔው የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ዶክተር ተብየው ያሾፋል እንደ ሌላው አገር ወገኖቻችንን በተቻለ መጠን ከአደጋ ለማትረፍ አውሮፕላን ልኮ ከየመን ማውጣት ሲገባው በዚህ ጭንቅ ጊዜ ለሱ ከየመን ስልክ እየደወሉ ድረሱልን ማለቱ እጂግ በጣም ያሳፍራል፣ የዛሬ አንድ ዓመት ተኩል ገደማ በሳውዲ አረቢያ ያሉ ወገኖቻችንን ህገወጦች ናቸው ብለው የማንም አረብ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ በማስለበስ እንደ በግ ወገኖቻችን የታረዱበት ዘግናኝ ጊዜ ሳይረሳን እንዲህ ደግሞ በየመን ባሉት ወገኖቻችን ላይ መቀለድ ያሳፍራል፡ ምነው አንዳርጋቸውን ለመያዝ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለየመን ደደብ ደህንነቶች ከፍለው አውሮፕላን አምጥተው ወደ ኢትዮጵያ የወሰዱት!!!
ለወያኔ የወገኖቻችን እልቂት የመብት ጠያቂዎችን የሕዝብ ጎራ መዳከም ስለሆነ ቴዎድሮስ አድኃኖም የስልክ ቁጥር የመላኩ ሸፍጥ የደስታ መግለጫ ያህል ነው። ለአንዳርጋቸው እገታ አይሮፕላን መላኩና ዶላር መፍሰሱ ለሥልጣናቸው ሥጋት መቀነሻ መሆኑ ነው። ውድቀታቸው ላይቀር አሣር ማብዛት ካልሆነ በቀር።

ወያኔ ለዜጎች ክብር ደንታ የሌለው ወንበዴ ስርአት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህ በጎሮቤት ሀገሮችና በተለያዩ አከባቢዎች የምናየው በዚጎች ወንድሞቻችና እህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍና በድል ሀገር ቤት ካለው አስከፊ ስርአት ጋር ተዛምዶ አለው የዜጎችን ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች ሚያከብር ስርአት ቢኖር በሌላውም ሀገር እንደዚህ አይነት አስከፊ ነገር አይኖርም ነበር፡፡ የእለት ሌብነታቸውን በማጧጧ ነገ ወደጥሉቁ ገድል ስንወረውራቸው ለሚያከትም ስልጣናቸው ቀን ከለሊት እንቅልፍ አተው ሲሰሩ ሲጨነቁ ሙሰኞችና ሌቦች ባለስልጣና አሁን የመን በዜጎች ላይ እየተፈጸፈመ ያለውን ግፍና በደል ያልሰሙም አሉ የሰሙትም ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ተኝተዋል ስልክ/ / ፀፈውም ያሾፍሉም ያላግጣሉ፡፡

No comments: