Monday, April 13, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ማንፌስቶውን በምሁራን ሊያስገመግም ነው

• ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በነገው ዕለት የፖለቲካና የትምህርት ጉዳይ ላይ ግምገማቸውን ያቀርባሉ
ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ማንፌስቶውን በምሁራንና በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሊያስገመገም እንደሆነ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ማንፌስቶው ያጠቃለላቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ልምድና እውቀት ያላቸው ምሁራን እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ግምገማ እንዲያደርጉና ሀሳባቸውን እንዲያጠቃልሉ የታቀደ ሲሆን በነገው ዕለት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነገ ማክሰኞ ሚያዚያ 6/2007 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖለቲካና ትምህርት ጉዳይ ላይ ግምገማ እንደሚያደርጉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልጾአል፡፡
የምርጫ ማንፌስቶውን ለምሁራንና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አቅርቦ ማስገምገም ያስፈለገው የተለያዪ የማህበረሰብ ክፍሎችን ሀሳብ እንዲያጠቃልል፣ የሰማያዊን አማራጭ ፖሊሲዎች ለህዝብ ለማድረስ እንዲሁም በደጋፊዎች፣ በመራጮችና በሌላው ህዝብ ዘንድም የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነም ተገልጾአል፡፡
በቀጣይነት በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ማንፌስቶው ያጠቃለላቸው ጉዳዮች ላይ በጉዳዮቹ ላይ እውቀት ያላቸው ምሁራን ግምገማ እንደሚደረግ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

No comments: