Monday, April 20, 2015

የዘር ማጥራት ዘመቻ ተጀመረ (ኦሮምያ ክልል)

በሰሜን ሸዋ ኦሮምያ ክልል ሸነን ወረዳ የአማራ ዘር ማጥራት ተጀመረ
ከቦታው የአይን ምስክር የሆኑት በላኩልን መረጃ መሰረት ከሳምንት በፊት ሁለት ከክልሉ የሚኖሩ ጓደኛሞች በአህያ ጉዳይ በተነሳ መለስጠኛ ግጭት አንደኛው የአንደኛውን ህይወት አጥፍቶ እጁን ለፖሊስ ሰጠ ግድያው ግን ከአማራው ጋር የተያያዘ አልነበረው::
ሀሙስ እለት ሚያዝና 8 2007 የወረዳው ፖሊስ በስፍራው ከዓርባ አመታት በላይ በአካባቢው ሰፍረው ይኖሩ የነበሩት በሞቶ የሚቆጠሩ የአማርኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል::
ሚያዝያ 9 2007 በአካባቢው ከ8 ዓመታት ወዲህ የሰፈሩ የኦሮሞኛ ተናጋሪ ህብረተሰብ በመንደሩን እየዞሩ ከ500 በላይ የአማርኛ ተናጋሪ የሆኑትን የህብረተሰብ አባላት ቤት እና ንብረት አቃጥለዋል ህጻናት ከቤቱ ጋር የተቃጠሉ ሲሆን ብዙ ሀብት እና ንብረትም ወድሟል::
በክልሉ ፖሊስ ታፍነው ወደእስር ቤት ከተወሰዱት አማራዎች ውስጥ አብዛኛው በእስር ቤት ያለጠያቂ እና አስታዋሽ እየተሰቃዩ ሲሆን ከእስር ቤት ማምለጥ የቻሉት አካባቢውን ለቀው ለመሸሽ ተገደዋል:: ከመንግስትም ሆነ ከፖሊስ የሆነ አካል በዚህ ጉዳይ ላይ ይህ ዜና እስኪጻፍ ድረስ ምላሽ የሰጠ የለም ::
ጥቃቱ ሚያዝያ 10 እና 11 2007 አዳሩን ተባብሶ ያድራል የሚል ስጋትም አለ :: ፖሊስ ለምን የአማርኛ ተናጋሪ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ያነጣጠረ እስራት እንደፈጸመ እና ይህንንም ተከትሎ የብዙ አማራ ቤቶች ሊቃጠሉ እንደቻለ ለግዜው ማወቅ አልተቻለም ወይም ምላሽ አልተገኘም ::
ይህ የዘር ማጥራት እርምጃ የሚመለከትው አካል አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጠው ከፍተኛ የደም መፋሰስ ሊያስከትል ይችላል:: በስፍራው ለአመታት የገነቡትን እና ያካበቱት ሀብት ንብረት ቤተሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲህ በቀናት ወድሞባቸው ያለ ጥላ ከለላ ደህንነታቸው በስጋት ውስጥ ወድቆ በሜዳ ላይ እንዲቀሩ ተገደዋል::
የሚመለከተው ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ይፈለግላቸው ::

No comments: