Friday, April 24, 2015

ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች ! በግጭቱ ሁለት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው ሲሞቱ 4 ቆስለዋል።


ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጨት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን » እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30 ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል።

newsይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋሉ በእርስ በእርስ ግጨቱ የተሳታፊ 4 ኢትዮጵያውያን በሰውነታቸው ላይ ከደረሰው መለስተኛ ጉዳት አገግመው በአሁኑ ሰዓት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በኢትዮጵያኑ መሃከል በሚከስት ግጨት በደም የተጨማለቀ በጠራራ ፀሃይ በሳንጃ አንጀቱ የተዘረገፈ ሬሳ መንፉሃ ውስጥ ማየት የተለመደ መሆኑን የሚገልጹ የአይን እማኞች የዛሬ አመት የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያኑ ላይ በወሰዱት እርምጃ በጉሩፕ ይከስት የነበረ የዕለት ተዕለት ዘግናኝ ትእይንት ለወራት ጋብ ብሎ ቢቆይም ሰሞኑንን በአዲስ መልክ በማገርሸቱ የአካባቢውን ነዋሪ ክፉኛ አስደንግጦል ብለዋል።

 
በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን መሃክል በሚከስት ግጨት ህይወቱ የሚያልፈውን ወገን ለማታደግ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ጋር በመተባበር ከአመት በፊት የጀመሩት ጥረት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድክመት መስተጓጎሉ የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች በአሁኑ ሰዓት ጭካኔ የተሞላበት የኢትዮጵያውያኑ የእርስ በእርስ ግጨት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንፉሃ በሚኖሩ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ላይ ስጋት መደቀኑ ይነገራል። ቀደም ብሎ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከግማሽ በላይ በባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን የሚናገሩ ወገኖች መንፉሃ እንደወትሮው በኑሮ ውድነት ሃገራቸው ውስጥ መኖር ተስኗቸው መሄጃ ባጡ ኢትዮጵያውያን ዳግም መጨናነቋን ይናገራሉ።
እልባት ያላገኘው ይህ የኢትዮጵያኑ የብሄር ግጨት በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ግምት ወስጥ በማስገባት በዚህ ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ስልክ በመደውል ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ ባይሳካም አባሳደር መሃመድ ሃሰን አፈጉባኤ አብዱላ ገመዳ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት ከመግባታቸው በፊት ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸውንና ኤንባሲው በግዜያዊነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር እይተመራ መሆኑን አንድ ስማቸውን መጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የኤንባሲው  ሰራተኛ ከስጡኝ መረጃ ማረጋጋጥ ፡ተችሏል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi ይህ ሰሞኑንን ሪያድ መንፉሃ እና አካባቢውን ሲያብጥ የከረመው ዘግናኝ የብሄር ግጭጥ ተዕይንት ነው ። ማሳሰቢያ ለዝግጀት ክፍሉ  ከዚህ በላይ ተያያዥ የሆነው የፍቶ መረጃ ቀደም ካለ የተወሰደ ሲሆን በቴክኒክ ምክንያት ከዚህ ዜና ጋር አባሪ በማደረግ መላክ ባለማቻላችን ይቀራት እየጠየቀን በወቅቱ የተከስተውን የቪድዮ ምስል በፊስ ቡክ የውስጥ መስመራችሁ መላኩን እንገልጻለን
source: zehabesha.com

No comments: