Wednesday, April 22, 2015

በሁሉም አቅጣጫ ፖሊስ በህዝብ ላይ እየተኮሰ ነው! በርካታ ህዝብ ታስሯል! ህዝብን በአስለቃሽ ጭስ እየበተኑ ነው!

ከመስቀል አደባባይ ወደ ለቅሶ ቤት ሰልፍ እየመሩ የነበሩት ወጣቶች ጨርቆስ አካባቢ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው፣ ፖሊስ ሊያስራቸው ሲል ህዝቡ አስጥሏቸዋል፡፡ መስቀል አደባባ ላይ ፖሊስ ወጣቶችን መደብደብ ጀምሯል! ህዝቡ እየደበደበ እየበተነ ነው! የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ዕጩዎች እየታሰሩ ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው ይድነቃቸው አዲስን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና አባላት ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አብዛኛዎቹ ስልካቸው አይሰራም፡፡ በርካቶች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ወጣች ላይ ድብደባው ቀጥሏል! ወጣቶች ተቃውሞ በማሰማታቸው ምክንያት በየ ቀበሌው ተደራጅተው የመጡት አዛውንቶች ከመሃላቸው እየወጡ ወጣቶች ሰብሰብ ብለው ድምጻቸውን ለማሰማት እድሉን አግኝተዋል! መስቀል አደባባይ ውስጥ በተለያዩ ቡድኖች ተደራጅተው ተቃውሞ የሚያሰሙት ወጣቶች እየተሰባሰቡ ሲሆን ፖሊስ እንዳይገናኙ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ወጣቶች ተቃውሞውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ኃይለማሪያም በሚናገሩበት ወቅት ወጣቶች ከሚያሰሙት ተቃውሞ መካከል
‹‹ውሸት ሰለች ሰለች!››
‹‹ዋ! ዋ! ዋ!››
‹‹ታርዷል ወገኔ!›› 
‹‹ታርዷል ወገኔ! ታርዷል ወገኔ!››
‹‹መንግስት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!›
‹‹መንግስት የሌለው የዚህ ብቻ!››
‹‹መንግስት የሌለው የዚህ ብቻ!››
‹‹ንጉሱ አርበኛ! መንግስቱ አርበኛ!›› እያሉ ኢህአዴግን እየተቃወሙ ነው
‹‹እኛን ከምትደብደብ ወንድሞቻችንን የፈጀውን ISIS ደብድብ››
‹‹ሌባ! ሌባ! ሌባ!ሌባ!››
‹‹የወንድሞቻችን ደም ይመለስ!››
‹‹ሶማሊያና ዳር ፉር ከምትልኩ ወደ ሊቢያ ላኩ!››
‹‹የፈሰሰው ደም የኢትዮጵያውያን አይደለም?››






No comments: