Thursday, April 23, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸው ታወቀ

• 100 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰልፈኛው ‹‹መንግስት በዜጎቻችን ላይ ለተፈፀመው አረመኔያዊ እርምጃ በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም›› በሚል ባሰሙት ተቃውሞ በርካቶች ተደብደበው ከተሳሩና ሰልፉ ካበቃ በኋላ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል በርካቶች እየታደኑ መታሰራቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ 

ሰልፉ ካበቃ በኋላ ታድነው ከታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ብሩክ የኔነህ ማታ 12 ሰዓር ላይ የተያዘ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና ከሰልፉ በኋላ ከ100 በላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተይዘው አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ታስረው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ጠና ይታየው፣ ይድነቃቸው አዲስና እስክንድር ጥላሁን የተባሉት የሰማያዊ ፓርቲው ዕጩዎች ሌሊት 6 ሰዓት ላይ ከአባላት ተለይተው መፈታታቸውን አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡

No comments: