Tuesday, September 17, 2013

አያልቅበት ወያኔ


አያልቅበት ወያኔ 

አሁንም ወደፊትም የህዝቡን ወኔ እየሰለቡ፣ የማይጨበጥ መላምት እየተናገሩ፣ 


ለህዝብ የ11 በመቶ የእድገት ወሬ እየሰለቁ ያደነቁሩናል። ነገር ግን የህዝቡ 

ኑሮ በ11 በመቶ ቁልቁል እየተንደረደረ የሚመገበው እንኳን ያጣ ምፅዋትን ጠባቂ 

ሆኗል። ገሚሱም ወደየበረሃዉ በመሰደድ የአውሬ፣ የባህር፣ የአሳ፣ የአዞ እራት እየሆነ 

የስንቱ ወላጅ አንጀት አሳርሮታል? 

ይህ ሁሉ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የጥቂት ከርሣሞች ማንአለብኝነትና 

አእምሮአቸው በንዋይ ፍላጎት የተደፈነ፤ በዚህም በእዝነ ልቦናቸው ታውሮ ከምስኪን 

ህዝብ ላይ እየነጠቁ የውጭ ባንኮችን እንዲያጨናንቁ ሆነዋል። ይህ ህዝብ ግን በቀን 

አንዴ እንኳን መመገብ እንዲያቅተው ተደርጎ ከቀን ወደቀን በየቤተ–ክርስትያኑ እና 

በየመስጂዱ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በልመና ተሰማርቶ እጅግ የሚያሳፍር ሁኔታ 

ላይ ደርሰናል። 

ከዚህ ሁኔታ በመነሳት አንዳንድ ተንታኞች ይህ ሁኔታ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ 

የኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኛው ለማኝ ይሆናል የሚል በመረጃ እያስደገፉ 

 እየተናገሩ ያለበት ሁኔታ ላይ መሆናችን በራሱ አስፈሪ ነዉ።

ታዲያ የዚች አገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ ምንድነው? ወደዳችሁም ጠላችሁም 

ወያኔ እንደሆነ አንድ ሰው የመብቱን ጉዳይ ሲጠይቅ የተለያየ ቀለም 

ይቀቡታል፤

★አንተ አሸባሪ

★አንተ አልቃይዳ

★አንተ ጎጠኛ

★ አንተ ኦ·ነ·ግ

★አንተ ግንቦት 7 ወዘተ እያሉ ማለቂያ ወደሌለዉ ማጎሪያ ይወረውሩታል። ለዚህም ማሳያ በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞችን ማየት በቂ ነው።


፨በሺዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በየበረሃው እስር ቤቶች ማየትም ቀላል የሆነበት ጊዜ መሆኑ አሳዛኝም ነው።

፨የስንቶቹም ቤተሰብ ልጅ ህይወት በወህኒ ማለፉን ቤት ይቁጠረው።


በተረፈ ሁሉን ቻይ ጌታ ለዚች ቅድስት ሃገር ይድረስላት!!

እኛንም መብታችንን የምንይቅ ያድርገን አሜን!!

No comments: