Saturday, September 7, 2013

አዲሱን ዓመት የጋራችን ለሆነችው አገራችን ኢትዮጵያዊ


አዲሱን ዓመት የጋራችን ለሆነችው አገራችን ኢትዮጵያዊ_ሕልም በማለም 

ስንጀምር እያንዳችን፣ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅብንን ‘ሀ’ ብለን የምንነሳበት 

እንዲሆንልን በማሰብ ነው። አገራችን የረሃብና ድህነት ሳይሆን፥ የጥጋብና 

ብልፅግና፣ የጦርነትና ሰብኣዊ መብት ጥሰት ሳይሆን፥ የዴሞክራሲና ነጻነት፣ 

የመናናቅና መጠላላት ሳይሆን፥ የመከባበርና መወዳጀት፣ የመሃይምነትና 

ድንቁርና ሳይሆን፥ የጥበበኝነት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መልካም ስምና ባሕል 

እንድታፈራ እንመኛለን።

አገራችን በሠላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብኣዊና ቁሳዊ ልማት፣ ትምህርት፣ ሳይንስና 

ቴክኖሎጂ፣ ኪነጥበብ፣ ስፖርት፣… በሁሉም ዘርፍ ዓለም የደረሰችበት ቁንጮ 

እንድትደርስ እናልማለን፣ እንመኛለን፣ ህልማችንን እውን ለማድረግም 

የሚጠበቅብንን በማድረግ የድርሻችንንእንወጣለን፡፡

No comments: