Tuesday, September 24, 2013

የአራት ኪሎን ህዝብ እናመሰግናለን


የአራት ኪሎን ህዝብ እናመሰግናለን



እውቅና ተችሮታል የተባለን የአንድነት የመስከረም 19 ሰላማዊ 

ሰልፍ ህዝብ አሳታፊ ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ከአንድነት ቢሮ በዛ 

ያሉ መኪኖች ለቅስቀሳ ወጥተዋል፡፡በአራት ኪሎና በአካባቢዋ 

የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመቀስቀስ ከወጡ መኪኖች መካከል 

የተወሰኑት በፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ 

ተደርገዋል፡፡


በመኪኖቹ ውስጥ የነበሩትን የአንድነት አባላት ፖሊስ ወደ 

ጣብያ ለመውሰድ ባደረገው ሙከራ ህዝብ መሰብሰብ ችሏል፡፡

ሁኔታውን በአንክሮ ይከታተል የነበረ ህዝብ ፖሊሶቹን ልጆቹን 

መውሰድ አትችሉም፣ሰልፉ እንደተፈቀደ እየታወቀ መቀስቀስ 

አትችሉም ማለታችሁ ህገ ወጥ ድርጊት ነው››በማለት እጅግ 

በሚያስደስት ሁኔታ ተከራክረዋል፡፡

አዎን ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈጸም በእኔ ላይ ካልሆነ ምን አገባኝ 

ብለን የምናልፍበት ዘመን ማብቃት ይኖርበታል ፡፡ይህንን 

ደግሞ የአራት ኪሎ ሰዎች ስለ ጀመሩት ከወዲሁ ምስጋናችን 

ይድረሳቸው፡፡

#millonsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ

No comments: