Wednesday, September 25, 2013

አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!


አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!


--------------------------


የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ! ጭቆና፣ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት ረገጣ፣ ድህነት፣ 

ሙስና፣ ጠባብ ብሄርተኝነት፣ እስራት፣ እንደ ባይተዋር ከአገርህ መባረርና ስደት 

እንደጠናብህ ራስህም ታውቀዋለህ፡፡ 
ይህን ሁሉ የህዝቡን ችግር፣ ፍርሃት፣ በመካከላችን ያለውን መከፋፈል አይተን ዝም 

ብንለው ያለ እቅድ እንደ ፍልፈል በቆፈረው መንገድና ጎዳና ሰላማዊ ሰልፍ ማገድ፣ 

አደባባዮቻችንን መከልከል፣ መልዕክተኞቹን ማሰሩን ቀጥሎበታል፡፡


አንደኛ መብቶችህን ተቀምተሃል፣ ሁለተኛ በእምነትህ ጣልቃ ገብቶብሃል፣ ሶስተኛ 


በብሄር ከፋፍሎሃል፣ አራተኛ በአገርህ በእኩልነት መኖር አልቻልክም፣ አምስተኛ 

በሙስና አገርህ ተመዝብራለች፣ ስድስተኛ ሰንደቅ አላማህን አዋርዷል፣ሰባተኛ አገርህ 

ወደኋላ ቀርታለች… ምን ቀረህ? እውነት፤ በወጣትነት ዘመንህ ይህን ሁሉ ችግር 

እያየህ ዝም ያልህ እንደሆነ እንደ ቀደመው ጊዜ ሁሉ ባይተዋር ሆነህ ትኖራታለህ፡፡ 

አሁንም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየማለ አይምርህም!


ጥሪውን እየሰማህ፣ ኑሮና ችግር፣ ጭቆና፣ ስደትና ሌሎች በርካታ ችግሮች 


እያንገበገበህ የቀረህ እንደሆነ ሰልፉ ላይ የተገኘነው ፈሪ፣ የአገር ሸክም፣ ሀሞት 

የሌለው እያልን በመሳለቅ አንምርህም፡፡ ጥሪውን የተቀበልክ እንደሆነ ግና እሁድ 

በጧት ቀደም ብለህ መስከረም 19 ወደ መስቀል አደባባይ ዝለቅ ከዛው እንገናኝ፡፡ 

33ቱ ፓርቲዎችና የተማረሩ የኢህአዴግ ካድሬዎችም ሳይቀር ከየ አቅጣጫው ወደ 

መስቀል አደባባይ ይዘምታሉ፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በአደባባዩ ተገኝተው 

ድምጣቸውን ለማሰመት ቃል ኪዳን ገብተዋል፡፡ 


እስከዛው ድረስ ቸር ይግጠመን!

No comments: