Thursday, September 12, 2013

ርዕዮት በወኅኒ ረሃብ ላይ ነች

በቃሊቲ ወኅኒ ቤት እሥር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከትናንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ማድረጓ ተገለፀ፡፡

በሕግ የታወቀላት መብቷ በትክክል እስካልተጠበቀ ድረስም በዚሁ እንደምትገፋ መናገሯ ታውቋል፡፡

የርዕዮት አባት አቶ ዓለሙ ጌቤቦ ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ወኅኒ የምትገኝ ልጃቸው የረሃብ አድማውን የጀመረችው ትናንት ረቡዕ፤ መስከረም 1/2006 ዓ.ም ነበር፡፡

ዛሬም አቶ ዓለሙ ሊጠይቋት ሲሄዱ መምጣት እንደሌለባቸውና ወደፊትም በሕግ ዕውቅና ያገኙ የእሥረኝነት መብቶቿ የማይጠበቁ እስከሆነ ድረስ በረሃብ አድማዋ እንደምትቀጥል እንደነገረቻቸውና እርሣቸውም ሆኑ ሌላ ሰው ምግብ በማመላለስ እንደይደክም እንዳሳወቀቻቸው ገልፀዋል፡፡

ርዕዮት ዓለሙ

ቪኦኤ እንደተረዳው ቀደም ሲልም ለአዲስ ዓመት ዋዜማ፣ ጳጉሜ 5/2005 ዓ.ም ርዕዮት ዓለሙን ለመጎብኘት ቃሊቲ ሄዳ የነበረችው እህቷ እስከዳር ዓለሙ በወኅኒ ቤቱ አስተዳደር ካለፈው ሣምንት ጀምሮ ጫና ሲደረግባት እንደቆየ አስታውቃ እንደነበረ እስከዳር ገልፃለች፡፡

በእስከዳር አባባል ካለፈው ሣምንት ጀምሮ የሚጠይቋትን የቤተሰቧን ስም ዝርዝር ለወኅኒ ቤቱ አስተዳደር እንድትሰጥ ተጠይቃለች፡፡

ርዕዮትም ጠያቂዎቿን ለይታ “እነዚህ ብቻ ይጠይቁኝ” የሚል ዝርዝር ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልነበረች ታውቋል፡፡

No comments: