• በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ላይ ያቀደውን ያሳካ ድርጅት የለም።
• ‘ክልል’ የሚለው ቃል ፌደሬሽን (ፌደራሊዝም) ለሚለው ተተኪ አይሆንም።
• የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ‘እኔ ብቻ፤ ለኔ ብቻ’ የሚለውን ሀሳብ ይጠየፈዋል፤ አጥር፥ ቅጥር ማበጀትን፣ አትድረሱብኝ ማለትን፣ የሰው ሳይሆን የውሻ ጠባይ ነው ብሎ በግልጽ ያስቀምጣል።
• … ‘ክልል’ የሚለው ቃል ባለፈው ከተነሱት፣ በሚቀጥለውም ከሚነሱት ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር አብሮ ቢነሳ ጥሩ ነው።
• ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ልማት ባለቤት ይሁን ወይም ለልማቱ የጥሬ ዕቃ አቅራቢ ነጋዴ ሊገባን አልቻለም።
• የኢትዮጵያ ሀብት የገዢው ፓርቲ የጥቅም ክልል መሆኑ እንዲቀር አሳስባለሁ።
• የፖለቲካ ስልጣን የያዘ ቡድን እንደገና የንግድ መዋቅሮች ላይ በሰፊው የሚሰማራበት ሁኔታ መቅረት አለበት።
• ኦሮሞ በኦሮሚያ ውስጥ ለዘላለም እንደሚኖረው ሁሉ ኢሕአዴግም በከለለው በስልጣኑ ለዘላለም ለመኖር ያቀደ ነው የሚመስለው።… እንደታናሽ ወንድም የምመክራቹ ብታርፉ ነው።
• በሚቀጥለው ምርጫ ኢሕአዴግ ስልጣኑን ለሚመረጠው ቡድን ማስረከብ አለበት። ይህን የምጠይቀው በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ብቻ ሳይሆን ‘በምትወዱት’ በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ስም እለምናችኋለሁ።
• የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ አንድ ሲሆን እሱም “ወላጆቼ በነፃነት እንድኖርባት ባስረከቡኝ ሀገሬ በነፃነት እኖር ዘንድ ልቀቁኝ። አትከልሉኝ፤ በገዛ ኢትዮጵያዬ የይለፍ ወይም ፓስፖርት አልጠየቅ፤ የኢትዮጵያን በረከት ያለአድልዎ ልመገብ። በሀገሬ ተስፋ ኖሮኝ ሠርቼ ልኑር፤ እራሴንም ተክቼ ልለፍ” ነው።
• ኢትዮጵያን ለመነጣጠል ሜትር፣ ገመድ ይዘው የሚነቀሳቀሱ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች እንዲያውቁ የምፈልገው፥ አንደኛ ኢትዮጵያን የሚያድናት እግዚያብሔር አለ፤ ሁለተኛ ታሪካችን ያድነናል። የአድዋ ጦርነት ላይ፣ የሱማሌ ጦርነት ላይ እንዲሁም ትላንት የባድመ ጦርነት ላይ ሕይወቱን ያጣው፣ ደሙ የፈሰሰውና አጥንቱ የተከሰከሰው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። ሊለያየን የሚሞክር ኃይል ከታሪካችን በላይ ሊሔድ አይችልም። ከኢትዮጵያ ላይ እንድ ጋት እንድትቆረጥ የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። አ!ን!ለ!ያ!ይ!ም!!

No comments:
Post a Comment