በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ደህንነት አድጋ ውስጥ እንደከተተ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሰኞ አስታወቀ።
መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ሪፕሪቭ ተቋም የሃገሪቱ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ጉዳይ ግምት ውስጥ በመክተት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻችና ይፋዊ ጥያቄን እንዲያቀርብ አስቧል።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት ተቃዋሚ ናቸው ባላቸው አካላት ላይ የሚወደውን እርምጃ ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሃላፊ ማያ ፎዓ (FOA) ገልጸዋል።
ዜጋውን ለማስፈራት የተለሳለሰ አቋም ይዟል የሚል ትችት የሚቀርብበት የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ግምት ውስጥ በመክተት ዜጋውን ለማስለቀቅ አፋጣኝ ጥያቄን ማቅረብ እንደሚገባው ሃላፊዋ አስታውቀዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው ይኸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ወር የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች ለአቶ አንዳርጋቸው መጻፊያ እስክርቢቶና ወረቀት እንዳይገባላቸው እገዳ መጣላቸውን አውስተዋል።
በዚህም የተነሳ አቶ አንዳርጋቸው የህግ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማቅረብ ያልቻሉ ሲሆን፣ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ የብሪታኒያ መንግስት በኩል አቶ አንዳርጋቸው የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።
ሁለቱ ሃገራት ባልፈው አመት ሰኔ ወር በጉዳዩ ዙሪያ ስምምነትን
ቢያደርጉም የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይችሉ ለብሪታኒያ መንግስት ማሳወቁን ሪፕሪቭ ማግኘት የቻለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
ጉዳዩ አሳስቦት እንደሚገኝ የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የብሪታኒያ መንግስት የችግሩ አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በመግባት አፋጣኝ እርምጃን እንዲወስድ አክሎ ጠይቋል።
ኢሳት
No comments:
Post a Comment