Wednesday, October 5, 2016

የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ናትናኤል ፈለቀ ታሰረ

(ምስል: ናትናኤል ከፍርድ ቤት ሲወጣ)
የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ናትናኤል ፈለቀ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 24 2009 ከስራ ሰዓት በኋላ ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ሙሉጌታ ከተባሉ ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ጋር በተለምዶስታዲየምተብሎ የሚታወቀው አካባቢ በሚገኝውላሊበላሬስቶራንት ውስጥ ተቀምጠውጮክ ብለውየቢሾፍቱ ጭፍጨፋ የመንግስት ጥፋት ነውእያሸበረ ያለው ራሱ መንግስት ነውበማለት አውረተዋል በሚል ምክንያት በፖሊስ ተይዞ ታሰረ፡፡ ናትናኤል እና ጓደኞቹ ዛሬ መስከረም 25 2009 ጠዋት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ የወንጀል ችሎት ቀርበው የዋስትና ጉዳይ ለማየት አሻራ ይስጡና ነገ መስከረም 26 2009 በድጋሚ እንዲቀርቡ ታዘው ወዳረፉበት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የካዛንችስና አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ (በተለምዶ 6ተኛ እየተባለ የሚታወቀው) ተመልሰዋል፡፡
ዞን ዘጠኝ አቋም
የናትናኤል እና የጓደኞቹ እስር አሁን አገሪቱ እየሔደችበት ያለውን መንገድ በሚገባ ያሳያል፡፡ ኢትዮጵያ ከጓደኞች ጋር ሰብሰብ ብለው የፖለቲካ ጉዳይ ማውራት የሚያሳስርባት አገር መሆኗም ለሁላችንም አሳዛኝ ነው፡፡ ስለዚህም ናትናኤልና ጓደኞቹ ሰውነታቸው ያስገኝላቸውን ሃሳባቸውን የመግለፅ መብታቸውን ከመጠቀማቸው ባለፈ ቅንጣት ታክል የሕግ መተላለፍ ያልፈፀሙ በመሆኑ አሁኑኑ ይፈቱ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡


No comments: