Sunday, October 2, 2016

በኢሬቻ በዓል ላይ በተነሳው ተቃውሞ በርካቶች ሞቱ

የኢሬቻ በዓል ግርግር

ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2009 .. በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ሞቱ፡፡ በዓሉ የሚከበርባት የቢሾፍቱ ከተማም ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናት፡፡
በዓሉ ላይ ተቃውሞ በመነሳቱ ሳቢያ የክልሉ አድማ በታች ሕዝቡ ላይ የአስለቃሽ ጭስ የተኮሰ ሲሆን፣ ጭሱን ለመሸሽ የሞከሩ በርካታ ሰዎች ገደል ውስጥ ገብተው ሞተዋል፡፡ ሆኖም ግን ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር በትክክል ማወቅ ባይቻልም፣ የሟቾች ቁጥር ግን ወደ መቶ ሊጠጉ እንደሚችሉ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
በዓሉን ለማክበር ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተሰበሰበው በበርካታ አሥር ሺዎች የሚቆጠረው ሕዝብ ተቃውሞውን ሲያሰማ ቆይቶ፣ በዓሉ ሳይከበር ቀርቷል፡፡ ሕዝቡ ‹‹ወያኔ በቃ!›› ‹‹ኦሕዴድ በቃ!›› በማለት ተቃውሞውን የገለጸ ሲሆን፣ አባገዳዎቹንም ከመድረክ ላይ ሲያስወርዷቸው በስፍራው የተገኙ የሪፖርተር ዘጋቢዎች ተመልክተዋል፡፡
በዓሉ በሚከበርበት ቦታም መሀከሉ ላይ ዛፍ የሌለው የክልሉ ባንዲራ ሲውለበለብ ታይቷል፡፡
ሕዝቡ በበዓሉ ላይ ሊጋቡ የመጡ ሙሽሮችንም የተቃውሞ ድምፅ በማሰማት ከመድረክ አስወርዷቸዋል፡፡
ተጨማሪ ዜናዎችን መረጃው እንደደረሰኝ አቀርባለሁ

No comments: