Sunday, October 2, 2016

ቶክሱ ከመጀመሩ በፊት ሁሉንም ጋዜጠኞች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ከተደረገ በኃላ የቶክስ ድምፅ ና የህዝቦች ዋይታ ና ጮኸት በርቀት ይሰማ ነበር

_91490985_mediaitem91490984

የጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ ስለተከሰተው ነገር ሲናገር ትናንት ማታ የነበረውን እና ዛሬ ጧት ከግርግሩ በፊት የነበረው ሰላም ተቃውሞ የነበረ እንደነበርና ነገር ግን ግርግሩና ቶክሱ ከመጀመሩ በፊት ሁሉንም ጋዜጠኞች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ መደረጉንና ጋዜጠኞቹ ከመሄዳቸው ወዳው የቶክስ ድምፅ የህዝቦች ዋይታ ጮኸት በርቀት ይሰማ እንደነበርና ቡሀላም ብዙ ቁስለኞችና አስክሬኖችን ማየታቸውን ገልጿል ለመሆኑ መጀመሪያ ጋዜጠኞችን በሙሉ ለምን ከዚያ እንዲወጡ ተደረገ? መጀመሪያ ግርግሩ ከመጀመሩ በፊት ከባድ መሳሪያዎች የፀጥታ ሀይሎች ለምን በተጠንቀቅቆሙ? ታንኩን የሚነዱት ወታደረችስ ለምን ፊታቸውን መሸፈን አስፈለገ? በደህናው ቀን ሲበሩ የነበሩትስ አምቡላንሶች ከግርግሩ በፊትና ቡሀላ ድራሻቸው ጠፋ ? ግርግሩን ጥቂት ሰዎች ጀመሩት ከተባለ ለምን አጠቃላይ ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ መልቀቅ አስፈለገ? እንዳጠቃላይ ይህ ጭፍጨፋ የተደረገው ቀድሞ በታቀደና ስልታዊ በሆነ መልኩ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየና ከላይ የተለቀቀው ጭስ ሆን ተብሎ ህዝቡ እንዲተራመስ በማድረግ ታጥቆ ለቆመው እና ህዝብን እንዲጨፈጭፍ ለታዘዘው አጋዚ ሰራዊት በር ምክንያትና ሽፋን መስጫ መሆኑንና አሁን በተግባር ተፈፃሚ እንዲሆን የተደረገ መሆኑን ያመላክታል  

metereyes

Source:satenaw

No comments: