Tuesday, October 11, 2016

ህወሃታዊያን ከ5000 ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያንን ለመክሰስ ወደ የተባበሩት መንግስታትና ወደ ሐያላን ሐገሮች የሚላክ ረቂቅ አዘጋጅቶ ጨርሶአል

TPLF (1)
መሆኑ የቅርብ ግዜ ትዉስታችን ነዉ የማስፈራሪያ አዋጅ ያልበገረዉን ህዝብ በድጋሚ በአስቸኩዋይ ግዜ አዋጅ ማፈን የሚቻል የመሰላቸዉ ህወሃታዊያን የመጨረሻ ሙከራቸዉን አድርገዋል።
በዚህ ከፍተኛ አጣብቂኝ ዉስጥ የሚገኘዉ ህወሃት የአስቸኩዋይ ግዜ አዋጁን ዋና ጥንስስ ወደ ዉጭ በመዘርጋት ቀንደኛ እና አመራር የሚላቸዉን 5000 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ለመክሰስ ወደ የተባበሩት መንግስታትና ወደ ሐያላን ሐገሮች የሚላክ ረቂቅ አዘጋጅቶ ጨርሶአል።
በዚህም መሰረት ግብጽና ኤርትራን ለህዝባዊዉ እንቢተኝነቱ መተባበር ግንባር ቀደም በማድረግ የሚያትተዉ ረቂቅ ከነዚህ ሐገሮች እርዳታ እየተደረገላቸዉ ህወሃታዊያንን ያሸብራሉ የሚላቸዉን ግለሰቦች ወደ ሚገኙበት ሐገር አቤቱታ ለማቅረብ እየተንጠራሩ ሲሆን።
የክስ ሂደቱን ኢንዲያግዝ የመረጃ ስብስቡ የመሐበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን መፈተሽ በህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ የተደረጉ የቅስቀሳ ንግግሮችን ማዳበል ወደ ሐገር ዉስጥ የተላኩ የገንዘብና የእቃ ሰነዶችን በተፈላጊ ግለሰቦች ስም ማዘጋጀትና ማቀናበር ከቤተሰብና ከተለያዩ የስርአቱ ቀኝ እጆችን ለምስክርነት ማዘጋጀት ዋነኞቹ መንገዶች ሲሆኑ በክሱ ዉስጥ በዋና ተፈላጊነት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች የኦነግ አመራሮች እንዲሁም በአሜሪካ እና በተለያዩ አለም ሐገራት ነዋሪ የሆኑ አክቲቪስቶች ጋዜጠኞችና ምሁራኖች ላይ የሚቀርቡ ክሶች ባጠቃላይ በመጠናቀር ላይ ናቸዉ።
ይህንን መረጃ የላኩልን ከፍተኛ ቁልፍ የህወሃት አመራር እንደገለጹልን እንደ ሐገር መሬዎች ከተቀመጡ ባለስልጣናት የማይጠበቅ የሐሳብ መንገድ ማለት ይህ የክስ ቅሌት ነዉ። ይህን ክስ አለም አይቀበለዉም የተባበሩት መንግስታት አትግደሉ እያለ በሚለምንበት በመጨረሽዋ በዚህች ሰሐት ገዳዮቹ እናንተ ጋር ነዉ ያሉት ስጡን ማለት ያሳፍራል! መሀበርእዊ ሚዲያን ተገን ያደረገ መረጃ ጭብጥ መሆን ካለመቻላቸዉ በላይ ክሶቹ የቀረቡበት ወቅትና ግዜ የህዝብ ጥያቄ በተፋፋመበት በመጨረሻዋ ግዜ ላይ መሆኑ ኪሳራዉን የበለጠ ያበረታዋል! በተለይ በተለይ ዲሞክራሲያዊ መብት በሚከበርባቸዉ እንደ አሜሪካ እና አዉሮፓ በመሳሰሉ ሐገራት ላይ በሚኖሩ ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ፋይዳ ቢስ ነዉ ሲሉ ትዝብታቸዉን አስቀምጠዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
(ልኡል አለም)

Satenaw

No comments: