ማክሰኞ
መስከረም 24፣
2009 አመሻሽ ላ
ከሁለት ጓደኞቹ ጋር
እሁድ መስከረም
22፣ 2009 በቢሾፍቱ
የኢሬቻ በዓል አከባበር
ላይ ከተፈጠረው
ጋር በተያያዘ
ስለ ጉዳዩ
በማውራት ሕዝብን አነሳስታችኋል
ተብለው ታስረው የነበሩት የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ እንዲሁም ሁለቱ ጓደኞቹ ናትናኤል ፈለቀ፣ ፀደቀ ድጋፌ እና አዲስዓለም ሙሉጌታ ዛሬ መስከረም 26፣ 2009 ረፋዱ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ ክሱ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋስትና አስይዘው ነገ መስከረም 27፣ 2009 ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡
የችሎቱን
ሒደት ስለ
ክሱ አጠቃላይ
ሁኔታ ያሳያልና
የችሎቱን ሙሉ ሪፖርታዥ
እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
ተከሳሾች፡-
1. ናትናኤል ፈለቀ
(በጠበቃ አቶ አምሃ
መኮንን ተወክለዋል)
2. ፀደቀ ድጋፌ እና
3. አዲስዓለም ሙሉጌታ
2. ፀደቀ ድጋፌ እና
3. አዲስዓለም ሙሉጌታ
መዝገቡ
የተቀጠረው፡-
1) የምርመራው መዝገብ
እንዲቀርብ (ትላንት አልቀረበም)
2) ምስክር መኖሩን ለማረጋገጥ (ትላንት አልተጠቀሰም)
3) የዐሥር ጣት የጣት አሻራ ተነስተው ሪከርድ እንዳለባቸው እንዲጣራ
2) ምስክር መኖሩን ለማረጋገጥ (ትላንት አልተጠቀሰም)
3) የዐሥር ጣት የጣት አሻራ ተነስተው ሪከርድ እንዳለባቸው እንዲጣራ
ዳኛ:
መዝገቡ
ቀርቧል፤ ሁለት ምስክሮች
ቃላቸውን ሰጥተው ቀርቧል፣
አሻራ የሚያነሱት
ስብሰባ ላይ ስለነበሩ
አልደረሰልንም ብሎ (ፖሊስ)
ዳኛዋ “ባይገልጹልን
ይሻል ነበር”
ብለው “እንዳይደገም”
አስጠንቅቀዋል፡፡
ጠበቃ
እና ተጠርጣሪዎቹ፡
1ና
የተጠረጠሩበት ጉዳይ የተባለው
ለእስር የሚዳርግ አይደለም፣
2ኛ አሻራ እንዲያመጣ ፖሊስ ተነግሮት አላመጣም፣
3ኛ ተጠርጣሪዎች ቋሚ አድራሻ ስላላቸውና ሠራተኞች በመሆናቸው ወደሥራ ገበታቸው በቶሎ እንዲመለሱ ዋስ ይሰጣቸው ብለዋል፡፡
2ኛ አሻራ እንዲያመጣ ፖሊስ ተነግሮት አላመጣም፣
3ኛ ተጠርጣሪዎች ቋሚ አድራሻ ስላላቸውና ሠራተኞች በመሆናቸው ወደሥራ ገበታቸው በቶሎ እንዲመለሱ ዋስ ይሰጣቸው ብለዋል፡፡
መርማሪ
ፖሊስ፡
“ድምፃቸውን ከፍ
አድርገው በአካባቢው የነበሩ
ሰዎች እንዲሰሟቸው
በማድረግ አንዳንድ ነገሮችን”
ተጠርጣሪዎቹ መናገራቸውን ጠቅሰው
የጣት አሻራ
ምርመራ እና የሞባይል
ስልካቸው ፎረንሲክ ምርመራ
ውጤት እስኪመጣ
ጣቢያ እንዲቆዩ
ጠይቀዋል፡፡
ዳኛ፡
“ይህ ለምን
ዋስትና እንደሚያስከለክል” ሲጠይቁ
ፖሊስ “ምስክር
ደልለው ያስጠፋሉ፣ ከአገርም
ሊወጡ ይችላሉ”
ብለዋል፡፡
ጠበቃ
እና ተጠርጣሪዎቹ፡
1ኛ
በሞባይል ወንጀል ተሠርቷል
ብሎ ፖሊስ
ከጠረጠረ በሕግ አግባብ
የሕግ ፈቃድ
ሊያገኝ ይገባ ነበር፣
2ኛ ምስክሮቹ የፖሊስ አባል ናቸው ከተባለ ይደለላሉ የሚለው ስጋት ሊሆን አይገባም፣
3ኛ ከአገር ሊወጡ ይችላሉ የሚለው አንድ ሰው በዋስ ለመውጣት የሚጠበቅበትን ቅድመ ሁኔታ ሟሟላት ብቻ ነው የሚጠበቅበት ብለዋል፡፡
2ኛ ምስክሮቹ የፖሊስ አባል ናቸው ከተባለ ይደለላሉ የሚለው ስጋት ሊሆን አይገባም፣
3ኛ ከአገር ሊወጡ ይችላሉ የሚለው አንድ ሰው በዋስ ለመውጣት የሚጠበቅበትን ቅድመ ሁኔታ ሟሟላት ብቻ ነው የሚጠበቅበት ብለዋል፡፡
ለዚህ
መርማሪው ሲመልስ፡
1ኛ
አሁን ወንጀል
እየተሠራ ያለው በሞባይል
ነው፣ መመርመር
አለብን፤
2ኛ ገና ቃል ያልተቀበልናቸው ሲቪል ምስክሮች አሉ በማለት አስተባብሏል፡፡
2ኛ ገና ቃል ያልተቀበልናቸው ሲቪል ምስክሮች አሉ በማለት አስተባብሏል፡፡
ዳኛ፡
ተጠርጣሪዎቹ
የ10 ጣት
አሻራ ዛሬ
እንዲሰጡ እና ነገ
መስከረም 27፣2009
ለብር አምስት
ሺሕ ብር
የሚበቃ ዋስ በማስያዝ
እንዲፈቱ ወስነዋል፡፡ በተጨማሪም
ተለዋጭ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ
ከአገር ውስጥ እንዳይወጡ
ተጠርጣሪዎቹ ታግደዋል በማለት
ችሎቱ ስራውን
አጠናቋል፡፡
አፕዴት
ጦማሪ ናትናኤል እና አብረውት የታሰሩት ሁለት ጓደኞቹ የ5 ሺህ ብር ዋስ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ፓሊስ ይግባኝ ለመጠየቅ ዛሬ ከሰአት በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዳቀረባቸው ተሰምቷል፡፡ ጠበቃቸው ባልተገኙበት ጉዳያቸው እንዲታይ ፍቃደኛ ባለመሆናቸውና ፍርድ ቤቱም ጠዋት የተወሰነ ነገር ላይ ፓሊስ ደግሞ ለፍርድ ቤት ያቀረበበት ምክንያት ግልጽ አለመሆኑን ገልጾ ነገ ጠዋት ጠበቃቸው በተገኙበት የዋስትና ክልከላውን ለማየት ለአዳር ቀጥሮታል፡፡

No comments:
Post a Comment