አዲስ አበባ መስከረም 29/2009 በመላ አገሪቷ
በታወጀው
የአስቸኳይ
ጊዜ
አዋጅ
የሚወሰዱ
እርምጃዎችና
የተከለከሉ
ጉዳዮች
ይፋ
ሆኑ።
የፌዴራል ጠቅላይ
አቃቤ
ህግ
የአስቸኳይ
ጊዜ
አዋጁን
አስፈላጊነት፣
ይዘት፣
የሚወሰዱ
እርምጃዎች፣
የተከለከሉ
ጉዳዮችና
ልዩ
ልዩ
ድንጋጌዎች
ይፋ
አድርጓል።
የአስቸኳይ
ጊዜ
አዋጁን
ለማስፈፀም
የተቋቋመው
ኮማንድ
ፖስት
አዋጁ
ተፈጻሚ
የሚሆንባቸውና
የማይሆንባቸውን
አካባቢዎች
በመለየት
ለሕዝብ
ይፋ
እንደሚያደርግ
የፌዴራል
ጠቅላይ
አቃቤ
ህግ
ጌታቸው
አምባዬ
ገልጸዋል።
እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ የአስቸኳይ
ጊዜ
አዋጁ
ተፈጻሚ
እንዲሆን
በተለያዩ
አካባቢዎች
በይፋም
ሆነ
በድብቅ
በህዝቦች
መካከል
መቃቃር፣
ጥርጣሬና
ግጭት
የሚፈጥሩ
እንቅስቃሴዎችን
ማድረግ
የተከለከለ
ነው።
በህዝቦችና ሃይማኖቶች
መካከል
ግጭትና
መቃቃር
የሚፈጥሩ
ፅሑፎች
ማዘጋጀትና
ማሰራጨት፣
ትዕይንትና
ምልክቶችን
ማሳየትና
መተግበርም
እንዲሁ።
ኮማንድ ፖስቱ የህዝብና
የአገርን
ሠላምና
ደህንነት
አደጋ
ላይ
ይጥላሉ
ያላቸውን
ማናቸውም
የመገናኛ
ዘዴዎች
መዝጋት
እንደሚችልም
አስታውቀዋል
አቶ
ጌታቸው።
አዋጁ ተግባራዊ እንዲደረግባቸው
በሚለዩ
አካባቢዎች
የመሰብሰብ፣
የመሰለፍና፣
የመደራጀት
መብቶችም
ሊታገዱ
ይችላሉ።
አዋጁን የሚተገብሩ
አካላት
በሁከትና
ብጥብጥ
የተጠረጠረና
የተሳተፈን
ሰው
ያለ
ፍርድ
ቤት
ትእዛዝ
በቁጥጥር
ሥር
ማዋልም
ይችላሉ።
በቁጥጥር ሥር የሚውሉ
ዜጎች
ተምረው
ይለቀቃሉ፣
ወንጀል
ፈጽመው
የተገኙም
በህግ
አግባብ
ይቀጣሉ።
አዋጁ ተግባራዊ በሚደረግባቸው
አካባቢዎች
የግለሰቦችን
መኖሪያ
ቤትና
ተሽከርካሪ
ያለፈቃድ
መበርበር
እንዲሁም
ሰዎችን
ያለምንም
ፈቃድ
አስቁሞ
መፈተሽና
መጠየቅ
እንደሚፈቀድ
ተናግረዋል።
በብርበራ የተያዙ
ንብረቶች
ወንጀል
ከተፈፀመባቸውና
ለመፈጸም
ከታሰበባቸው
ሊወረሱ
ወይንም
ለባለንብረቱ
ሊመለሱ
የሚችሉበት
ሁኔታ
መኖሩንም
አመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት የሰዓት
እላፊ
አለመታወጁን
የገለፁት
አቶ
ጌታቸው፤
ነገር
ግን
ለህዝብ
ይፋ
በተደረጉ
አካባቢዎች
ሊታወጅ
እንደሚችል
አስታውቀዋል።
ኮማንድ ፖስቱ አደጋ የተጋረጠባቸውና
አስፈላጊ
ናቸው
ያላቸውን
መንገዶችና
ተቋማት
ሊዘጋ
ይችላል፤
ለአደጋ
ተጋላጭ
ለሆኑ
ተቋማትም
ልዩ
ጥበቃ
ያደርጋል
ነው
ያሉት።
አደጋ በተጋረጠባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ
ዜጎችን
ደህንነት
ለመጠበቅ
ሲባል
ሰዎችን
ለተወሰነ
ጊዜ
በተወሰ
ቦታ
የማቆየት
እርምጃ
ሊወሰድ
እንደሚችልም
ተናግረዋል።
ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ
ቦታ
እንዲቆዩ፣
ወደ
ተወሰነ
አካባቢ
እንዳይገቡ
ወይም
ከተወሰነ
ቦታ
እንዲለቁ
ለማዘዝ
እንደሚችልም
ጠቁመዋል።
አዋጁ ተግባራዊ እንዲደረግባቸው
በሚለዩ
አካባቢዎች
ዜጎች
የጦር
መሳሪያ፣
ተቀጣጣይ
ነገርና
ስለት
ወይም
እሳት
የሚያስነሱ
ነገሮች
ይዞ
መንቀሳቀስም
የተከለከለ
ነው።
ኮማንድ ፖስቱ የአስተዳደር
እርከኖች
በፈረሰባቸውና
በተዳከመባቸው
አካባቢዎች
ከክልሉና
ከህዝቡ
ጋር
በመተባበር
የማቋቋም
ስራ
እንደሚሰራ
ገልጸዋል።
የሚከሰተውን አደጋ ጥልቀት
ስፋት
መሰረት
በማድረግም
በመደበኛ
የህግ
ማስከበር
መከላከል
የማይመለሱ
ከሆነ
ተመጣጣኝ
እርምጃ
ሊወስድ
እንደሚችል
አስታውቀዋል
አቶ
ጌታቸው።
የፍሬ ነገርና የሥነ ሥርዓት
ህጎች
ሊታገዱ
እንደሚችሉም
አክለዋል።
አዋጁ ተግባራዊ በሚደረግበት
አካባቢ
የሚገኙ
ዜጎች
የአስቸኳይ
ጊዜ
አዋጁን
ማክበርና
ለተፈጻሚነቱ
የመተባበር
ግዴታ
እንዳለባቸው
ጠቅሰው፤
ይህን
የማያከብሩና
የማይተባበሩ
አዋጁ
በሚፈቅደው
አግባብ
እንደሚቀጡ
ተናግረዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን
ተግባራዊ
ማድረግ
የሚያስችል
ደንብና
መመሪያ
ይዘጋጃል።
አዋጁ በመላ አገሪቷ የታወጀ
ቢሆንም
ተግባራዊ
የሚደረግባቸውን
አካባቢዎች
ኮማንድ
ፖስቱ
ለሕዝብ
ይፋ
ያደርጋል።
No comments:
Post a Comment