Sunday, October 2, 2016

በኢሬቻ በዓል ላይ በተነሳው ተቃውሞ ከ 300 ሰዎች በላይ በወያኔ ታጣቂዎች ተገደሉ

ኢሬቻ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ ለማውገዝ የግድ ኦሮሞ መሆን አይጠበቅም፡፡ ያሳዝናል፤ ያናድዳል፡፡ ለነጻነት በሚደረግ ትግል የንጹሐን ዜጎች ሞት የሚጠበቅ ቢሆንም ባዶ ቄጠማን በእጃቸው ይዘው ከአምላካቸው ለአገራቸው ሰላም ሲለምኑ በነበሩ ሰዎች ላይ ይህን ዓይነት መቅሰፍት ሲወርድ በምን ቃል መግለጽ ይቻላል? 
በዚህች አገር ላይ በዓልን በፌሽታና በደስታ እንዲያከብሩ የተፈቀደላቸው ከተከዜ ማዶ ያሉ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን በግልጽ እያየን ነው፡፡ 
ለሞቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ፤ በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ተወላጆች ከተጎዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጎን በመቆም አጋርነታችን የምናሳይበት ከዚህ ጊዜ በላይ የለም፡፡ 
ትግላችን መራር ቢሆንም ማሸነፋችን ግን ጥርጥር የለውም!!

No comments: