Friday, March 27, 2015

ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ …

በአለም ላይ ሰዎች መብታቸውን አስከብረው በነፃነት ሀሳባቸውን እንዲገልፁ እና እንዲኖሩ በአለም የተደነገገ ህግ ነው፡፡ ይህ ህግ/መብት/ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አይሰራም እረ እንደውም አይታሰብም፡፡ በእያንዳንዱ ግለሰብ የኢህአዴግ ካድሬዎችን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡ በሀገሪቱ ፖሊሶች ወታደሮች እና ባለስልጣኖች በእየመስርያ ቤቱ በየቤቱ የሚደርስበት በደል እና የመብት እረገጣ ይህ ነው የማይባል ነው፡፡ ሰው በሰውነቱ እንኳን የማይከበርበት ሀገር ነው፡፡ ህዝብን በዘር በመከፋፈል በመጨቆን እና እርስ በእርስ በማባላት እነርሱም ስልጣናቸውን በመጠቀም በማን አለብኝነት ያሻቸውን እያደረጉ ሀገሪቱን ተቆጣጥረዋል፡፡ ታዲያ ወገን እሰከመቼ ነው በኢህአዴግ/ወያኔ/ መንግስት እና ግብረአበሮቹ ጭቆና እና የመብት እረገጣ ተንበርክከን እንደ ዜጋ በሀገራችን መብት ሳይኖረን የምንሰቃየው? እና ወገኖቼ ይህን ዘረኛና ጨካኝ አንባገነን መንግስት በጋራ ሆነን ልንታገል እና ከስር መሰረቱ ልንገረስሰው ጊዜው አሁን ነው ለዚህም ደሞ በጋራ ሆነን በፅኑ ልንታገለው ይገባል፡፡

ጎህ መፅሔት

No comments: