Saturday, March 28, 2015

ነፃነት ያለትግል አይታሰብም

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከዛሬ 22 ዓመታት በፊት እራሱን ለጭቁኑ ህዝብ አሳልፎ ለመስጠት እና በደርግ መንግስት በህዝቦች ላይ የሚያደርሰውን ጭቆናና የዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ለመቅረፍ ብሶት የወለደው ኢህአዴግ ብሎ እራሱን የሰየመው ቡድን ይሄው 22 ዓመታት ሙሉ አስበውት እንደመጡት ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን በማስጠበቅ የህዝቦችን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ ሀገሪቱን በግል ጥቅም እና አገዛዝ በሚያመቻቸው ብልሹ አሰራርና ፖሊሲ ቆርሰውና ከፋፍለው ሀገሪቱን ከማትወጣው አዘቅት ውስጥ እየከተቷት ይገኛሉ፡፡

ህውሀት/ወያኔ/ ባስቆጠራቸው 22 ዓመታት ውስጥ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ተዋደውና ተከባብረው ከመኖር ይልቅ እርስ
በእርስ መጋጨት በሀገሪቱ ላይ ታይቶ የማይታወቅ የኑሮ ውድነት የሚስኪኑን ገበሬ መሬት በግድ እየተነጠቀ ለህውሃት ካድሬዎች እና ለውጭ ኢንቨስተሮች መስጠት የትምህርት ጥራት ማነስ የሙሁራንና የተማሪዎች በግድ የወያኔ ደጋፊ እንዲሆኑ ማስገደድ ያለበለዚያ የመማር ዕድል እንደማያገኝ በሚያነሱአቸው የመብት ጥያቄዎች በወያኔ ካድሬዎች እየታፈኑ ለሰው ልጆች ማሰቃያ ባዘጋጁት ማጎሪያዎች ውስጥ ፍፁም ሰብአዊነት በጎደለው ጭካኔ ስቃይ ይፈራረቅባቸዋል ብሎም በየአረብ ሀገራቱ ከመድፈር እስከ ከፎቅ መወርወር ድረስ ያለውን መከራ እየተቀበሉ ያሉት ሴቶች እህቶቻችን የመሳሰሉትን ዘርዝረን የማንጨርሳቸው መጥፎ ድርጊቶች የሀገሪቱ ገፅታዎች ሆነዋል እየሆኑም ነው፡፡ የዚህች ቅድስት ሀገር ትንሳኤ እና ሰላም የምትሹ የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆይ ነፃነት ያለትግል በጭራሽ አይታሰብም ስለዚህም ይህች ሀገር ከጥቂት ወያኔዎች መኖሪያነት ወደ 90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መኖሪያነት ለመቀየር መታገል የግድ ነው፡፡

ለዚሁም በኢትዮጵያ ትንሳኤ ወያኔን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያለ እየታገለ ካለው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ጎን መቆም አለብን እላለሁ፡፡

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ


Firezewed Berhanu

No comments: