Monday, March 30, 2015

የወያኔ ስልጣን ጥማት ለማርካት እጅግ ጭካኔና ግፍ የተሞላበት ስርአት ከብዙዎቹ በጥቂቱ

1.የሀገሪቱን ህዝብ በጎሳ፣ በሐይማኖትና በድንበር እንዲጋጩ ማድረግ
2.የተማረውንም ሆነ ያልተማረውን በጥቅማ ጥቅም ወይም በግዴታ የፓርቲው አባል ማድረግ
-የተማረ ከሆነ ስራ ለማግኘት ወይም የስልጣን እርከን ለማሳደግ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለፓርቲው አባል ለሆነ ሰው ተሻለ ዕድል በመስጠት ያልተማረውን ደግሞ በጦር ሰራዊት በማሰማራት በሕገ-መንግስቱ መሰረት ከየተኛውም ፓርቲ ነፃ መሆን አለባቸው ነገር ግን በወያኔ አገዛዝ የሀገሪቱን ህልውና ሳይሆን የወያኔን ስልጣን ጠበቃ አድርጓቸዋል ወይም የወያኔ ቃታ ሳቢ አድርጓቸዋል፡፡
3. ጭኩን ሆነ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት
4. ፍርድ ቤቶችን መቶ በመቶ ለራሳቸው እንዲቆሙ ማድረግ
5. ፓርላማውን አሻንጉሊት ማድረግ
6. የተለያዩ የመገናኛ ቡዙሀን እንዲያሰራጩ በማድረግ እነዚህን በመሳሰሉ ትልልቅ መንገዶችን በመዘርጋት ወያኔ የስልጣን ጥማቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ይሄ ሁሉ ግፍ የመረረው ወጣት ዛሬ ሀገሩ ሰርቶ መኖር ሳይችል ሲቀር በስደት ላይ ይገኛል፡፡ ገሚሱ ደግሞ በጥይት ዶፍ ተበሳስቶ አልፏል፡፡
የወያኔ የጭቆና አገዛዝ መቼ ይሆን የሚያበቃው?
እኛስ መቼ ይሆን የማንሰደደው?

ሊዲያ ወልዴ ዮሐንስ
ጎህ መፅሔት

No comments: