Thursday, March 5, 2015

በአገር ሙሉ ጀግና ሞልቶ ወያኔን ጀግና አሉት።

ሀገራችን የጀግና ደሀ አይደለችም ጀግኖች የሞሉባት ሀገር ናት። በየተሰለፍንበት መሰኩ አለምን ያስደመመ ጀግኖች ያፈራች አገር ነች።በትምህርቱ ዘርፍ እስከ ሳይንቲስት የደረሱ የትምህርት ጀግኖች አሉ። በሰዕሉ እስከ የአለም ሎሬት የደረሱ የስእል ባለሞያ ጀግኖች አሉን። በስፖርቱም እስከ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሌያና የአለምን ክብረ ወሠን የሚሰብሩ ጀግኖች ልጆችን ያፈራች አገር ነች። በኪነ ጥበቡ ጥግ  ድረስ የደረሱ የኪነ ጥበብ ጀግኖች አሉን። በምርምሩም አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚፈጥሩ ድንቅዬ እና ብርቅዬ  ልጆች አሉን። መቼም ጀግና አጥተን የጀግና ደሀ ሆና አታዉቅም አገራችንን የሚያኮሩዋት ጀግኖች አሉዋት የጀግናም ጀግና።
ወያኔን ጀግና አሉት
Addis Berhanuወያኔን ጀግና አሉት! በTPLF የትግል ድርሻ ያለው እና ታጋዮች ጭምር ተወዳጅ የሆነውን ታጋይ ኃየሎም አርአያ በትግል ግዜ ሁሌም ካጠገባቸዉ እንዳይለይ የሚፈልጉት በቆራጥነቱ እና በችሎታዉ ታጋዬች በሙሉ የሚተማመኑበት ሀየሎም አርአያ ቀድሞም የጀኔሪል ማእረግ የተሰጠዉ ሰራዊቱ በጣም ስለሚወደዉ አና ስለሚያከብረዉ የተሸበሩት የTPLF መሪ ተብዬዎች  ነገ ትልቅ ቦታ እንደሚይዝ እና የወያኔዎችን ኃሳብ ሊቀበላቸዉ እንደማይችል ስለሚያቁ  ያንን ከባድ ጊዜያቶችን አሳልፎ የመጣዉን ታጋይ እየተዝናና ባለበት ሰአት አንድ ተራ የወያኔ ካድሬ በበላዮቹ TPLF ሰዎች ትእዛዝ ተሰጥቶት ሳያስበዉ በመሳሪያ ተኩሶ በመምታት ገደለውታል። ይሄ ነዉ የወያኔ ጀግንነት?
በትግሉ ሰአት አብሮአቸዉ የነበሩት የትግራይ ሰዎች ትግሉንም በድል ያጠናቀቁትን  የትግራይ ልጆች ከድል በኋላ  ከወያኔ ጋር የሀሳብ ልዩነት በመኖራቸዉ ብቻ በድብቅ  አየተከታተሉ ከሰላሳ ስድስት ሺህ  በላይ ታጋዬችን የገደሉ እንግዲህ እዚህን ገዳዬች ነዉ ጀግኖች የምትሉት?
ሀዉዜን ላይ የወረደዉ የቦብ ዝናብ በደርግ ባለስልጣን ዉስጥ ሆኖ ትዕዛዝ ያስላለፈዉ አና ይህንን ምስኪን ሕዝብ ለድብቅ አላማቸዉ የሰዉ ሀይል ለማግኛ ተበዳይ ለመምሰል ወደ ሀዉዜን ገበያ የወያኔ ወታደር በሙሉ ገብተዋል ተብሎ እንዲነገር  አስደርገዉ የትግራይን ሕዝብ ዳር ቆመው ያስፈጁትን ወያኔን ጀግና አሉት።
አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ምንም የጦር መሳሪያ ባልያዙ ንፁሀን ዜጎጀ ላይ የፈሪ ዱላ አንደሚባለው በያዙት መሳሪያ  ያለምንም ርህራሄ ህዝቡን የፈጁት ነዉ እንግዲህ ጀግና የምትሉን?
ጋንቤላ ላይ ከመሬታችን አታፈናቅሉን በመሬታችን መኖር እንፈልጋለን ብለዉ መሬታችንን ለባዕዳን አትስጡብን ብለዉ ተቃዉሞ ባሰሙት ንፁሁን የጋቤላ ተወላጆች ላይ ብረት አንስግቶ የፈጀዉና በግዳጅ ከመሬታቸዉ አፈናቅሎ ለባድ የሚሰጠዉን ነው ዉያኔን ጀግና የምትሉት?
በአኝዋከ ህዝብ ላይ መሬታቸዉን በመፈለግ የአኝዋከ ህብረተሰብን ዘግናኝ በሆነ መልኩ የዘር ማጥፋት እልቂት ከደረሰ በኋላ በጅምላ ወደ አንድ ጉድጓድ የከተተዉን ነዉ ጀግና ብላቹ የምትጠሩት?
በኦጋዴን ዉሰ በሱማሌ ተወላጆች ህብረተሰብ ላይ በአየር ቦምብ በማዝነብ የዘር ማጥፋት የፈፀመዉን እና እንደ ሃውዜን ውስጥ እንዳደረጉት ጭካኔ የተሞላበት ስራቸውን የደገሙትን ነዉ ጀግና ያላችኋተው?
አንቦ  ላይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሰረት ተቃዉሞ የወጣዉን የአምቦ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የታጠቀ ወታደር አሰማርቶ ተማሪዎችን መግደል ነዉ እንዴ ወያኔን ጀግና ያሰኘዉ?
ባህር ዳር ላይ ስለሀይማኖት ብለዉ የወጡት ሰላማዊ ሕዝብ ላይ አነጣጥሮ ተኩሶ መግደል ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ ታድያ ጀግና ያሰኛቸዉ ምንድን ነዉ?
ብዕር የያዘ ጋዜጠኛ አንተ አሸባሪ ነህ ብሎ ወደ እስር መጣል ነዉ ጀግንነት? ወይስ የፖለቲካ ሰዎችን ባላቸዉ የፖለቲካ አቋም በመፍራት ብቻ የአሸባሪ ታፔላ እየለጠፉ ወደ ወይኒ መወርወር ነዉ ጀግንነት? ወይስ የተማረዉንም ያልተማረዉንም ሰዉ በኛ መስመር ግባ ካልገባህ መኖር አትችልም ብለዉ ማዋከብ ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ?
ጀግና ማለት በፍቅር ታግሎ  በፍቅር የሚያሸንፍ  ነዉ። ጀግና ማለት ከባርነት ቀንበር አላቆ ነፃነትን የሚያወርስ እና በነፃነት እንዲኖሩ ማድረግ ነዉ።ጀግና ማለት ስራዉ  ከሚናገዉ በበጠ ጏልቶ የሚታይ እና በሰዉም ዘንድ ተቀይነትን ያገኘ ነዉ።
ጀግና ማለት እንደ ዉሻ ላበላዉ የሚጮህ ሳይሆን ለእዉነት የቆመ ለእዉነት የተሸነፈ ለእዉነት የሚኖር እሱ ነዉ ጀግና። መሳርያ ስለያዘ ብቻ ከኔ በላይ ማን አለብኝ ብሎ እየተኯሰ ሰላማዊ ሰዉን የሚገል እሱ ጀግና ሳይሆን አረመኔ ነዉ አረመኔን ደሞ ጀግኖች ያጠፉታል።
ጀግና ማለት ለነሱ የታጠቀ ኃይል በሰላማዊ ሰዉ ላይ ተኩሶ መግደል ከመሰላቸዉ፡ ጀግና ማለት ለነሱ ብዕር የያዙትን ብዕራዉያንን በብረት አስረዉ ማሰቃየት ከሆነ፡ ጀግና ማለት ለነሱ የፓለቲካ ሰዎችን በአአስከፊ ቅጣት መቅጣት ከመሠላው፡ እኔ ግን እላለዉ እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ ፈሪ እና እውቀት የጏደላቸዉ ናቸዉ። እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ የጨነቃቸዉ ናቸዉ እላለዉ። ፈሪና የጨነቀዉ ሰዉ የሚያደርገዉን ድርጊት እያደረጉት ያሉት።
ጀግናማ ፍቅርን አስተማሪ ነዉ። ጀግናማ ለህዝብ የቆመ ነዉ። ጀግናማ ለሆዱ ያልቆመ ነዉ። ጀግናማ ኢትዮጵያዊው ነው።
To Addis Berhanu
03.03.2015
Email- berhanu.addis@yahoo.com

No comments: