Thursday, March 5, 2015

ፍትህ ለሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች

አየር ሐይልን ከድቶ በይፋ ግንቦት 7 የተቀላቀለው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ታናሽ ወንድም ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ መሆኑ ታወቀ የሚል ዜና ከሠሞኑ ማስነበቤ ይታወሣል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በዛሬው እለት ሠይፈ መዘነን ጉዳይ ለማጣራት እንደሞከርኩት ይህንን ዜና እስካጠናከርኩበት ሠዓት ድረስ ሠይፈ መዘነ የሻለቃ አክሊሉ መዘነ ታናሽ ወንድም በመሆኑ እና ሻለቃ አክሊሉ አየር ሃይልን ከድቶ ግንቦት 7 መቀላቀሉን ተከትሎ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ እየተሠቃየ ይገኛል፡፡
በጣም አሣዛኙ ጉዳይ በወያነ መርማሪዎች ድብደባ እየደረሠበት ያለውን ሠይፈ አዘነ ጉዳይ ስለሠብዓዊ መብት ጥሠት ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ዝምታ ነው በተለይም ሻለቃ አክሊሉ መዘነ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ከድቶ ግንቦት 7 ሲቀላቀል ከፍተኛ መነጋገሪያ እንዲፈጠር አድረገው የነበሩት የግንቦት 7 አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠትን ለተመለከተ ሠው በጣም የሚያሣዝን ነው ይህንን ስል በሠይፈ ላይ እየደረሠ ያለው ጉዳይ የተለየ ሆኖ ለሠይፈ ብቻ እንጩህ ማለቴ ሳይሆን ቢያንስ ወንድሙ ግንቦት 7 ስለተቀላቀለ በገዢው ፓርቲ ደህንነቶች በቤተሠቡ ላይ እየደረሠበት ያለውን ጉዳይ ለመላው የሐገራችን ህዝብ እናሳውቅ በሚል ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ምንአልባት ነገ ግንቦት 7 ለመቀላቀል ላሠቡ ግለሠብ ፍራች ይፈጥራል የሚል ከሠብዓዊነት በታች የወረደ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያለው ሠው ካለ በጣም የሚያሳፍር የወረደ አስተሳሰብ ይመስለኛል፡፡
ፍትህ ለኢትዮጵያዊያን
ፍትህ ለሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች
‪#‎ሁኔአቢሲኒያ

No comments: