Tuesday, September 6, 2016

ውስጣችን አዝኗል፤ አዝነን ግን መቀመጥ የለብንም #ግርማ_ካሳ



"ሁሉም ለኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ለሁሉም" እያለ ጽሁፉን የሚያጠቃለል ወጣት አለ። ብሎገር ነው። የሰማያዊ ፓርቲም አመራር ነው። የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ። በኦሮምያ በተነሳው እንቅስቃሴ አፍነው ወሰዱት። መጻፉ መጦመሩ በጽሁፉ በጦማሩ ለአገሩና ለህዝቡ በመቆርቆሩ ወንጀለኛ ተባለ። ዮናትን ተስፋዬ።
አዎን የዛሬይቱ የሕወሃት ኢትዮጵያ አገራቸውን የሚወዱ ዜጎንች ወደ ወህኒ የሚወረወሩባት ኢትዮጵያ ናት።
በቂሊንጦ እሥር ቤት በካፌቴሪያ እሳት ይነሳል። ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ እሳትን መካላከልና እስረኞችን ማዳን ሲሆን፣ እሥር ቤት ሃላፊዎች እሳት ፊኦት ለፊታቸው እየመጣ ያሉ እስረኞች እሳቱ እንዳያመልጡ አገዱ። ተኮሶባቸው።በ እስር ቤቱ ብዙ እስረኞች ሞቱ።ገዢው ፓርቲ ራሱ 23 እስረኞች እንደሞቱ አምኗል። ከዞያም በላይ ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ።
ከነዚህ እስረኞች መካከል አንዱ የሆነው የዮናት ተስፋዬ እናት / ሙጪት ተካ ለአሜሪካ ሬድዮ VOA ስለ ልጃቸው እንዲህ ተናግረዋል
"......... ልጄ በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ አላውቅም በእሳት ተቃጥሎ ይሙት ወይም በጥይት ተመቶ ይሙት አላውቅም..... በየማረሚያ ቤቱ ዞርኩኝ....ሆስፒታልም ሄድኩ ልጄን ግን ማግኘት አልቻልኩም....እኔ ሃገሬ የት ነው። የት እንሂድ ? ለማን አቤት እንበል? ልጄ የታሰረው ለህዝብ ሲል ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ። የአ. ህዝብስ ለምን ዝም ብሎ ያያል "
የሗእሃት እሥር ቤቶች እስረኞችን ቶርቸር በማድረግ የምታወቁ ናቸው። "ማረሚያ ቤት" ነው የሚሏቸው ግን የቶርቸርና የስቃይ ቦታዎች (torture chambers) ናቼው። በዚያ ያሉ ፍጹም ጨኻንን ኢምንት ሰብአዊነት የሌላቸው ናቸው። ቤተሰበ የስረኞችን ጉዳይ ለመጠየቅ ሲሄዱ መደብደብና መሰደብ ነው ያተረፉት። የአገዛዙ ባለስልጣናት ነገሩን አጣርተው ለሕዝብ ያለዉን ነገር ማስወቅ ሲገባቸው፣ የዜጎች ሕይወት ተራ ነገር የሆነ ይመስል " ይሄን ያህል ሞተ" ብሎ እንደ አንደ ተራ ዜና ከማወራት ዉጭ የፈየዱት ነገር የለም። እነርሱ እሺህ ምንም ነገር አያደርጉ፣ ግን ቢያንስ ቤተሰብ አወቆ መደረግ ያለበትን እንዲያደረጉ መረጃዎች ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።
እንግዲህ ወገኖቼ ተመልከቱ እየሆነ ያለውን። ራሳችንን እስቲ በዮናታን እናት ቦታ እናድርግ። በአገራችን፣ በምድራች በዚህ ሁኔታ ገዢዎች በደል ሲፈጽሙብን በአገራችን አገር እንደሌለን ስንሆን አያሳዝንም።
ወገኖቼ አገራችንን ተነጥቀናል። በአገራችን አገር እንደሌለን እየተቆጠርን ነው። በዮናትን ተስፋዬ በቤተሰቡ ላይ የደረሰው በብዙዎች ላይ የደረሰ፣ ወደፊት በሁላችንም ላይ የሚደርስ ነው። ህወሃቶች ለኛ ሕይወት ደንታ የላቸውም። ብንሞት፣ ብንሰደድ፣ ብንፈናቀል፣ ብናነባ ደንታቸው አይደለም። ትናንሽ ፍርፋሪ ስለሚወረወሩልን የጠቀሙን መስሎን ከሆነ ተሳስተናል። እነርሱ በጣም ዘረኛ የሆኑ ከራሳቸው ጎጥ ዉጭ ማየት የማይችሉ፣ በጣም ክፉና መሰሪ የሆኑ፣ በሕግ ስም ህዝብ የሚያሸብሩ የጥፋት ሃይሎች ናቸው።
በተለይም የአዲስ አበባ ህዝብ በየወረዳው መነቃነቅ አለብን። ህወሃት መወገድ አለበት። እየገደሉን፣ እየሞትን እስከ መቼ ነው የምንኖረው። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን። ውስጣችን አዝኗል፤ አዝነን ግን መቀመጥ የለብንም። ያንን ካደረግን በሐዘን ላይ ሐዘን መቀጥሉ አይቀሬ ነው። ግን ዳግም እንድናዝን የሚያደረገን ነገር እንዳይከሰት ከአሁኑ ማድረግ እንችላለን።


No comments: