የዓለም የጤና ድርጅትን (WHO) ለመምራት በዕጩነት ሲወዳደሩ የነበሩት ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ከውድድሩ ውጪ ተደረጉ፡፡ የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና የአሁኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ ከፍተኛ ገንዝብ በመርጨች የምረጡኝ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሆኖም ዶክተሩ ከውድደሩ ውጭ መሆናቸው ግድ ሆኗል፡፡
ለውድቀታቸው እንደ ምክንያት ተደርገው ከተቀመጡት ጉዳዮችች መካከል ግንባር ቀደሙ እሳቸውና ጓዶቻቸው የሚመሩት ነፍሰ ገዳይ ስርዓት ሲሆን፣ ስርዓቱ በንጹኃን ላይ የሚፈጽመው ግፍ ነጥብ ሊያስጥላቸው እንደቻለ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ የህወሓት መንግስት አምባገነን እና ገዳይ ስርዓት መሆኑን ጠቅሰው ለዓለም የጤና ድርጅት አቤቱታቸውን ያቀረቡ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳይመረጡ የመጎትጎት ስራ መስራታቸው ታውቋል፡፡ የዶክተሩ ስርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እየፈመ ያለው ግፍ ለከት የለሽ መሆኑን የጠቀሱት እነዚሁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ለዶክተሩ ውጤት ማጣት የአንበሳውን ድርሻ መጫወታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎቹ በተጨማሪ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውን እና በማኅበራዊ ሚደያ ላይ ዶክተሩ እንዳይመረጡ የተቃውሞ ፊርማ ያሰባሰቡ ሀበሾች ለድርጅቱ ያቀረቡት አቤቱታ ለዶክተር ቴዎድሮስ ከውድድሩ ውጭ መሆን ሌላኛው ምክንያት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዶክተሩ ያገኙት ውጤት እጅግ አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ከዚህ በፊት እንደሳቸው በዚህ የውጤት ደረጃ ተዋርዶ የወጣ ዕጩ ተወዳዳሪ እንዳልነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ ዶክተር ቴዎድሮስ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ የሚለጥፉት ነገርም ለውድቀታቸው ምክንያት ከሆኑ አብይ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በሀገሪቱ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ መንግስታቸው በንጹኃን ዜጎች ላይ የሚወስድው የኃይል እርምጃ ተገቢ እና ተመጣጣኝ መሆኑን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲገልጹ የሚስተዋሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም፣ የስርዓታቸውን ግድያ መደገፋው እና ማበረታታቸው በውጤታቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ግድያን የሚደግፍ አንድ ሚኒስትር የዓለም የጤና ድርጅት መሪ ለመሆን መወዳደሩ ያስገርማል›› ሲሉ ታዛቢዎች ገልጸዋል፡፡
የዶክተር ቴዎድሮስ ከውድድሩ መባረር የህወሓት መንግስት እና ባለስልጣናቱ በዓለም ዓቀፍ መድረክ ምን ያህል እየተገለሉ እንደሆነ እንደሚያመላክት የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ አምባገነኖቹ ባለስለልጣናት በደም የጨቀየ እጃቸውን ይዘው የትኛውም ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ውስጥ መስራት እንዳማይችሉ የዶክተሩ ውጤት አመላካች ነው ብለዋል-አስተያየት ሰጪዎቹ፡፡ ዶክተር ቴዎድሮስ ቦታው ላይ ለመቀመጥ በጣም ቋምጠው የነበረ ሲሆን፣ ከእሳቸው በተጨማሪም ስርዓቱ በእሳቸው መመረጥ ከፍተኛ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ሲሰናዳ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቀድሞ መንግስት ባለስልጣናት የነበሩ ሰዎች ዛሬ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በተለያየ ዘርፍ እንደሚሰሩ የጠቀሱ ታዛቢዎች፣ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የደርግን መንግስት በመወንጀል የሚታወቁት የህወሓት ባለስልጣናት እንዲህ ዓይነቱን ዕድል አለማግኘታቸው የውርደታቸውን ለከት አልባነት እንደሚያሳይ ታዛቢዎቹ ይገልጻሉ፡፡ በደርግ መንግስት የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኃላፊ የነበሩት ኮ/ል ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ፣ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በአማካሪነት እንደሚሰሩ ይታወቃል፡፡

BBN news
No comments:
Post a Comment