Wednesday, September 21, 2016

የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ #አርብ_ጥቁር_ልብስ_የመልበስ ፕሮግራም አዛጋጅቷል በሚል ፍርሀት ስብሰባውን ነገ በማቋረጥ በመጪው እሁድ ተሐድሶ በማለት በተለያዩ አካባቢዎች የዘፈን እና የግብዣ ፕሮግራም እየተዘጋጀ ነው።

በኢትዮጵያ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት መምህራንን በመሰብሰብ አይኑን በጨው በማጠብ ጥቅምት ድረስ ጠብቁኝ ሲል የነበረው ገዢው ህወሀት ኢህአዴግ በመምህራኑ በደረሰበት "በስብሰባው ፀጥ የማለት ተቃውሞ" እና አርብ በመምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቃውሞ ተጠርቷል በማለት ከነገ በዃላ ስብሰባው እንደማይቀጥል ለማወቅ ተችሏል።
የመምህራን ድምጽ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ከታማኝ ምንጮች በደረሰው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ #አርብ_ጥቁር_ልብስ_የመልበስ ፕሮግራም አዛጋጅቷል በሚል ፍርሀት ስብሰባውን ነገ በማቋረጥ በመጪው እሁድ ተሐድሶ በማለት በተለያዩ አካባቢዎች የዘፈን እና የግብዣ ፕሮግራም ያዘጋጀ ሲሆን የእሁዱ ጥሪ ነገ ለመምህራኑ እንዲነገር ለሕወሐት ካድሬዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ነገ የመጨረሻው ቀን በመሆኑ የተነሳ ተቃውሟችን እሰካሁን እየሄድንበት ባለው መንገድ የሚቀጥል ሲሆን ተጨማሪ አዳዲስ ነገሮች ካሉ የምንገልፅ ይሆናል።

No comments: