Sunday, September 25, 2016

የመንግስት ወታደሮች በነቀምቴና ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝ አቅራቢያ ሰላማዊ ወጣቶችን መግደሉን ቀጥለውበታል

ተሐድሶ ላይ ነኝ ያለው  መንግስት በኦሮሚያ ሁለት አሻንጉሊት መሪዎችን ካስቀመጠ በኋላም በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርገውን ግድያ አጠናክሮ ቀጥሏል::
መንግስትን በሰላማዊ መንገድ መቃወም ምላሹ ሞት በሆነባት ኢትዮጵያ ዛሬም በነቀምት አስደንጋጭ ኹነት ተከስቶባታል:: እንደመረጃዎች ከሆነ ይህ በፎቶ ግራፉ ላይ በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በጥይት ተበሳስቶ የተገደለው ወጣት የተገደለው በነቀምት ነው:: ኢፋ አዲሱ የተባለው ይኸው ወጣት ሰላማዊ ሰው ቢሆንም የሕወሓት ወታደሮች ግን ስሙን ከተቃውሞ ጋር በማያያዝ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ገድለውታል::
screen-shot-2016-09-25-at-12-57-08-pm
በተያያዘ ደግሞ ትናንት ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝ አቅራቢያ በአጋዚ ወታደሮች በጥይት አንገቱ ላይ በጠሱት፤ ወደ ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ባሕር ዳር ተወሰደ 3 የፈጀ ቀዶ ጥገና ቢደረግለትም ደም በሆስፒታሉ በአለመገኘቱ ሕይወቱ መትረፍ አልቻለም።


No comments: