Tuesday, July 21, 2015

በእነ ወይንሸት ላይ የተጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ


መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ የቆዩት እነ ወይንሸት ሞላ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ከተፈረደላቸው በኋላ ሰኔ 22/2007 አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ነበር፡፡ ይሁንና የልደታ ፍርድ ቤት ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቄራ ፍርድ ቤት በእነ ወይንሸት ላይ የወሰነውን ውሳኔ በማፅናት አቃቤ ህግ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ከውጭ ሆነው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን ‹‹የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አልተቀበልክም›› በሚል ተጨማሪ አንድ ወር የተፈረደበት ማስተዋል ፈቃዱ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ማስተዋል ፈቃዱ የ3 ወር እስሩን የጨረሰ በመሆኑ በዛሬው ዕለት ከእስር ይለቀቃል ተብሎ ይገመታል፡፡

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር 

No comments: