Tuesday, July 14, 2015

ለውድ የዞን9 ነዋርያን

ለ445 ቀናት በእስር ላይ የሚገኙት ጦማርያን ሰኞ ሃምሌ 13 ለ31ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ፡፡ የቀረበባቸውን ማስረጃ መከላከል አለባቸው ወይስ የለባቸውን የሚለውን ለመበየን የሚሰየመው ፍርድ ቤት ምን ምን ማስረጃዎቸን ጎብኝቶ እነደሚወስን መረጃዎችን ለመስጠት ይህ የሁነት ገጽ ተከፍቷል ፡፡ ገጹ ከሃሙስ እስከ ቅዳሜ ባሉት ሶስት ቀናት የተለያዬ የሚቀርቡባቸውን ማስረጃዎች ለዞን9 ነዋሪያን ያቀርባል፡፡
እነዚህን ማስረጃዎች ማወቅ የዞን9 ጦማርያን ይፈቱ የምንልበትን ምክንያት ለማጠናከር ይረዳናልና ሁላችሁም የዞን9 ነዋሪያን እንድትሳተፉ የሚመጡ መረጃዎቸን እንድታስተላልፉ እና እንድታጋሩ ከዞን9 ጦማርያን እንዲሁም ከሌሎች ብዙ ያለምንም ምክንያት የታሰሩ ወዳጆቻችን/ችሁ ላይ ቀረበ የሚባለውን ማስረጃ በማጋራት የፍትህ ስርአቱን እንድንፈትሽ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ስለሚያገባን እንጦምራለን!
ዞን9

No comments: