Thursday, July 16, 2015

“እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር 3 “

"በግንቦት ሰባት አማካኝነት የተሰጠው የሽብር ስልጠና ማስረጃዎች "
የሽብርተኛነት ስልጠናውን ለተከሳሾች ሰጥተዋል ተብለው በማስረጃነት የተጠቀሱትን ድርጅቶች ማየትም የማስረጃዎቹ አስደንጋጭ ይዘት ነው፡፡ በፍርድ ሂደቱ ወቅት ከሳሽ ስልጠና የሰጡ ተቋማትን እና ስልጠናው አይነት በዝርዝር እንዲያቀርብ ሲጠየቅ አድበስብሶ ያለፋቸው የስልጣና ይዘቶችና አሰልጣኞችም በሰነድ ማስረጃው ተካተዋል፡፡ የሽብር ሰልጠና ሰጡ የተባሉት ድርጅቶች ዝርዝር
Civil rights defenders ( CRD) , The floke bernadotte academy , the Swedish institute , Swedish international development cooperation agency ( SIDA), the open society foundation , tactical thec , Kenya Media council ( KMC) , Article 19 , freedom house , National endowment for democracy , IREX , united nations higher commission for human rights, amnesty international , committee to protect journalist (CPJ) , eastern and southern Africa Journalists association ( ESAJA) , Rhoedeb Journalism university and African institute for governance with integrity ይገኙበታል ፡፡
የክሱ የሰነድ ማስረጃ ውስጥ ከትምህርት ተቋማት እስከ ማህበራት እና አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ( የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ) ቀርበው ሲታይ የሰነድ ማስረጃውን አስገራሚ ያደርጉታል፡፡ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የመሰሉ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሽብር የተከሰሱት ተከሳሾችን የሽብር ስራ ለማጣራት እና ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ እነዚህንም ሰነዶች ይመረምራል፡፡
Source: Zone9

No comments: