Thursday, May 7, 2015

የወያኔ አሳፋሪ ትርዒት በወላይታ ሶዶ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ!

ዘንድሮ ምርጫውን ለማጭበርበር ገዢው ፓርቲ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚጠበቅበትን ሁሉ ቀድሞ መዘጋጀቱ የሚታወቅ ቢሆንም ዛሬም ግን ከስጋት ነፃ ሊሆን አልቻለም። ለምርጫው ያሰጉኛል ያላቸውን ሁለት ህብረ ብሄር ፓርቲዎች ማፈረሱን፣ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች እንዳይወዳደሩ ማገዱን፣ ህዝብ ስጋት እንዲገባው ማዋከቡን፣....... ምርጫውን ለማጭበርበር ከተጠቀመባቸው ስልቶች ጥቂቶቹ ናቸው። ህዝብ እንደ መረረው የተገነዘበው ወያኔ ዛሬም ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን ህገ-ወጥ ድርጊቱን በካድሬዎቹ በኩል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እየፈፀመ ይገኛል። ለምርጫ ቅስቀሳ ወላይታ ሶዶ የሄዱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የወያኔ ካድሬዎች ችግር ሲፈጥሩ ነበር። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመኪና እየዞሩ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት የወያኔ ካድሬዎች በሞተር እየተከተሉ ፖስተሮችን ከመኪና ላይ ሲቀዱ ነበር። ይህ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነኝ ለሚል አካል በጣም አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት ነው።
ሰማያዊን ይምረጡ!

No comments: