ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ሳምንታት በውዴታና በግዴታ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ ወጣቶች አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸውን አምለጠው የመጡ ወጣቶች ለኢሳት ተናግረዋል።
አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ወጣት “በመጀመሪያ የወረዳው ባለስልጣናት ለስብሰባ ጠርተውን መንጃ ፈቃድና ልዩ ልዩ ስልጠና ስለምንሰጥ ከነገ ጀምሮ ተነሱ አሉን። እኔና 50 የምንሆን ጓደኞቼ በማግስቱ አዋሽ አርባ በሚባል ቦታ ተወሰድን። ከዚያ እንደደረስን ጸጉራችሁን
ተላጩ ተባልን። 1 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ሌላ ካምፕ እንደምንወሰድ ተነገረን። እስር ቤት መሆኑን ያወቅነው በሁዋላ ነው። ከተለያዩ ክልሎች የተሰባሰቡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አሉ። ከካምፕ ለማምለጥ ሲሞክሩ ውሃ የወሰዳቸው ወጣቶች አሉ።
ከእስረኞች መካከል ተማሪዎችም አሉበት” ብሎአል።
ከምርጫው ጋር በተያያዘ ረብሻ ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለን መታሰራችንን ያወቅነው በሁዋላ ነው የሚለው ወጣቱ፣ ከአካባቢው ጠፍተው የሚመጡ ወጣቶችን ለማደን እንቅስቃሴ በመጀመሩ ለመደበቅ መገደዱን ገልጿል።
በክልሎች ወጣቶች ለስልጠና በሚል ሰበብ የሚያዙ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ግን አብዛኞቹ ወጣቶች የተያዙት በሃይል ነው።
Source: Ethsat
No comments:
Post a Comment