ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም ክስ ተመስርቶበት የ6000 ብር ዋስትና ተጠይቆበት ብሩ ተከፍሎ ከእስር እንዲለቀቅ ከተደረገ በኋላ በደህንነቶች ታፍኖ የታሰረው የሰማያዊ አባል ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው በአንድ ክስ ሁለት ቀጠሮ ተሰጠበት፡፡ ቴዎድሮስ በትናንትናው ዕለት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ለግንቦት 18 ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡
በተመሳሳይ ክስ ዋስትና ተፈቅዶለት ውጭ ሆኖ እንዲከራከር ለዛሬ ተቀጥሮ የነበር በመሆኑ እንዲቀርብ ቢጠይቅም ፖሊስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡ የቴዎድሮስ አባት ልጃቸውን ወክለው ለመቅረብ ቢጥሩም እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል፡፡ በመሆኑም በሌለበት ለግንቦት 24/2007 ዓ.ም እንዲቀርብ ተቀጥሮበታል፡፡ ቴዎድሮስ ዋስትና ተሰጥቶት ውጭ ሆኖ እንዲከራከር የተፈቀደለትምሆነ ከተፈታ በኋላ እንደገና የታሰረው መስቀል አደባባይ በነበረው ሰልፍ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ሲሆን በአንድ ክስ ሁለት ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡

በ6000 ብር ዋስ ወጥቶ እንዲከራከር የዋስትና መብት ከተፈቀደለት በኋላ በደህንነቶች ታፍኖ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኘው ቴዎድሮስ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment