በደቡብ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በሀድያ ዞን ጌጃ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢ የሆኑት አቶ በየነ ጫፎን የደኢህዴን ካድሬዎች የንግድ ቤታቸውን በማሸግ እንዳሰሯቸው በሀድያ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል አቦቼ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ ለታዛቢነት ያቀረባቸውን ሰዎች ስምና አድራሻ ለደኢህዴን ካድሬዎችና ደህንነቶች አሳልፎ ስለሚሰጥ ታዛቢዎች በስፋት እየታሰሩና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነም አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ሚዛን ቴፒ ላይ መንግስት ‹‹የሸፈቱ ሰዎች አሉ›› በሚል ሰራዊቱን በማስፈሩ ምክንያት በህዝብና በሰራዊቱ መካከል ውጥረት እንደተፈጠረና ነዋሪዎች ግጭት ይነሳል በሚል ከአካባቢው እየለቀቁ እንደሚገኙ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ስጋት ውስጥ ታዛቢዎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ምርጫውን ለመታዘብ እንዳይችሉ እንቅፋት እንደተፈጠረባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡ በስጋቱ ምክንያት አካባቢው እስኪረጋጋ ምርጫው እንዲራዘም ቢጠይቁም ደኢህዴን ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡
Source: Semayawi Party- Ethiopia
No comments:
Post a Comment