ምርጫ የሚደረገው የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ወቅት ሁሉም ፓርቲዎች ወንበሩን ለመያዝ ይፎካከራሉ ማለት ነው። ህዝብም ሁሉም ፖለቲካ ፓርቲ የሚያቀርቧቸው አማራጭ ፖሊሲዎች በክርክርና በቅስቀሳ ወቅት በመገምገም ይበጀኛል የሚለውን ይመርጣል ማለት ነው። ወያኔም ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነኝ ብሎ የሚያምን መንግስት እንደመሆኑ መጠን ይህን የመከተል ግዴታ አለበት። ሬድዋን ሁሴን ለሚዲያዎች በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሰማያዊ ፓርቲ ለገዢው መንግስት አደጋ ስለሆነ ህዝብ ሊኮንነው ይገባል ብለዋል። ይህ በውነቱ በጣም አሳፋሪ ከአንድ የሃገር መሪ የማይጠበቅ ቀሽም የወረደ አስተሳሰብ ነው። ምክንያቱም ተቃዋሚ ፓርቲ ጠንክሮ ወጥቶ እንዲህ ተፎካካሪ ሲሆን ገዢው መንግስት ብርታት መስጠት ይጠበቅበታል። ህዝብ ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲን መኮነን ያለበት ለገዢው ፓርቲ ስጋት/አደጋ ስለሆነ ሳይሆን ለሃገራችን አደጋ ቢሆን ነበር። ህዝብ ደግሞ እያሸበረው ያለው ወያኔ እንጂ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳልሆነ ጠንቅቆ ያውቃል።
ድል ለሰፊው ሕዝብ!
No comments:
Post a Comment