ዛሬ 12 ሰዓት የጀመረው ምርጫ በወከባ ተጀምሯል፡፡ ኢህአዴግ ካድሬዎች መራጮቹን በመጠርነፍ እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሆነ አዲስ አበባ ውስጥ ከምርጫ ጣቢያ 03 የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ታግደው በማርፈዳቸው ወረቀት ሳይቆጠር ምርጫው ተጀምሯል፡፡ በተመሳሳይ በወረዳ 15 ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ‹‹አትገቡም!›› ተብለው ወከባ እንደደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ተገኔ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ወረዳ 6 ምርጫ ጣቢያ 20 መራጮች ጣት ላይ የሚደረገው መርገጫ ቀለም የሚለቅ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ቀለሙ የሚለቅ መሆኑን ገልጸው ቃለ ጉባኤ እንዲያዝላቸው ቢጠይቁም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝና አንዳንዶቹ በወከባው ምክንያት በቦታው አለመገኘታቸውን ዕጩዎቹ ገልጸውልናል፡፡

በደቡብ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በሀድያ ዞን ጌጃ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢ የሆኑት አቶ በየነ ጫፎን የደኢህዴን ካድሬዎች የንግድ ቤታቸውን በማሸግ እንዳሰሯቸው በሀድያ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል አቦቼ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ ለታዛቢነት ያቀረባቸውን ሰዎች ስምና አድራሻ ለደኢህዴን ካድሬዎችና ደህንነቶች አሳልፎ ስለሚሰጥ ታዛቢዎች በስፋት እየታሰሩና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነም አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ሚዛን ቴፒ ላይ መንግስት ‹‹የሸፈቱ ሰዎች አሉ›› በሚል ሰራዊቱን በማስፈሩ ምክንያት በህዝብና በሰራዊቱ መካከል ውጥረት እንደተፈጠረና ነዋሪዎች ግጭት ይነሳል በሚል ከአካባቢው እየለቀቁ እንደሚገኙ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ስጋት ውስጥ ታዛቢዎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ምርጫውን ለመታዘብ እንዳይችሉ እንቅፋት እንደተፈጠረባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢዎች ገልጸዋል፡፡ በስጋቱ ምክንያት አካባቢው እስኪረጋጋ ምርጫው እንዲራዘም ቢጠይቁም ደኢህዴን ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ለሰማያዊ ፓርቲ ሊታዘቡ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግቢ የኢህአዴግ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ ከሆናችሁ ከትምህርት ትባረራላችሁ›› ብለው ስላስፈራሯቸው በቦታው እንዳልተገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሌሎች ታዛቢዎችም በትናንትናው ዕለት የታዛቢነት መታወቂያ ከተሰጣቸው በኋላ በደረሰባቸው መከባ ምክንያት በቦታው እንዳይገኙ ተደርገዋል ተብሏል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን አብዛኛው የምርጫ ጣቢያዎች አንድ ለአምስት የጠረነፉት የኢህአዴግ ካድሬዎች ለሌላው ሰው እየመረጡ እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አደነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀው ‹‹አሁን እንፈታዋለን!›› ቢሉም እስካሁን አልተፈታም ብለዋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን አብዛኛው የምርጫ ጣቢያዎች አንድ ለአምስት የጠረነፉት የኢህአዴግ ካድሬዎች ለሌላው ሰው እየመረጡ እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አደነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀው ‹‹አሁን እንፈታዋለን!›› ቢሉም እስካሁን አልተፈታም ብለዋል፡፡
ሲዳማ ቦርቻ ወረዳ ደግሞ 26 የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን እየመለሱ ሲለቀቁ፣ ሶስቱ መታወቂያን አልመልስም በማለታቸው አሁንም እንደታሰሩ ናቸው፡፡ በጉራጌ ዞን የም ልዩ ወረዳ ደግሞ 48 የሰማያዊ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡
ወሎ መርሳ ውስጥ የኢህአዴግ ካድሬዎች 1ለ5 ለጠረነፏቸው መራጮች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ በቦታው ሌሎች መራጮችንም እያስገደዱ መሆኑ ተገልጾአል፡፡ ዋድላ ወረዳ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎችም የብአዴን ካድሬዎች በግዴታ እያስመረጡ መሆኑን ከታዛቢዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በተመሳሳይ ሰሜን ቆቦ 09 ቀበሌ የቀበሌው ሊቀመንበር መራጮች ብአዴንን መምረጥ እንዳለባቸው እያስገደደ መሆኑን መራጮቹ ገልጸዋል፡፡
ባሌ ውስጥ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ የኦህዴድ ታዛቢዎች ብቻ ገብተው እንዲታዘቡ ተፈቅዶላቸዋል ተብሏል፡፡
ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ ሱልጣን ኤገኑ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ታስረዋል፡፡ ታዛቢዎች ቤታቸው ተከቦ ወደ ምርጫው እንዳይሄዱ ተደርገዋል፡፡ ካድሬዎች በር ላይ ቆመው መራጩ ማንን መምረጥ እንዳለበት እንደሚናገሩ ተገልጾአል፡
አዲስ አበባ ውስጥ የወረዳ 6 የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ችግሮች እንዲቀረፉ ብንጠይቅም መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡ ታዛቢዎቹ ከተሰለፈው ህዝብ በስተጀርባ እንዲቀመጡ በመደረጋቸው ካርድ የሚሰጡትን፣ ቀለም የሚቀቡትንና ሌሎቹንም ተግባራት መከታተል እንዳልቻሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
መድረክን በመወከል አዲስ አበባ ወረዳ 19 ላይ የቀረቡት አቶ አብርሀም ሳልህ በ146 የምርጫ ጣቢያ ላይ ያሰማራኋቸው ታዛቢዎቼ ጠዋት ላይ ወደ ጣቢያዎቹ ሲያመሩ ደብዳቤ ካላመጣችሁ ብለው እንደመለሱባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን ኢህአዴግ ሁለት ሁለት የራሱን ታዛቢ ያለደብዳቤ አስቀምጧል ይላሉ፡፡
የወረዳ 20 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ አቶ እስክንድር ጥላሁን ታዘን ነው ያሉ የፖሊስ አባልና አንድ ሲቪል ‹‹መኪናህ ይፈለጋል፡፡ መንጃ ፈቃድህን ስጠን›› በሚል ከቦታ ቦታ እንይነቀሳቀስ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ የአቶ እስክንድር ታዛቢዎች ወደ ምርጫ ጣቢያው ከሌሊቱ 10ና 11 ሰዓት አካባቢ በሚሄዱበት ወቅት ‹‹ከፓርውና ከምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ካላመጣችሁ›› በሚል እንዳይገቡ መደረጋቸውን ገልጾአል፡፡ የሌሎች ፓርቲዎች ታዛቢዎች ደብዳቤ እንዲያመጡ ያልተጠየቁ ሲሆን አቶ እስክንድር ምርጫ ቦርድ ደውለሎ በጠየቀበት ወቅትም ‹‹የሰጠናቸው መታወቂያ ብቻ በቂ ነው፡፡ ደብዳቤ አያስፈልግም›› እንደተባለ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ደብዳቤ ካላመጣችሁ›› ተብለው የተጉላሉት የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች አብዛኛውን ሂደቶችን መታዘብ አልቻሉም ተብሏል፡፡
No comments:
Post a Comment