Wednesday, May 20, 2015

የአቤል ኤፍሬም ህይወት አደጋ ላይ መሆኗን ቤተሰቦቹ ገለፁ

በደህንነቶች ተይዞ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት አቤል ኤፍሬም ህይወት ከፍተኛ አደጋ መሆኗን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቤተሰቦቹ ዛሬ ግንቦት 12/2007 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ አቤል ኤፍሬም ከተኛበት ምኒልክ ሆስፒታል ለመጠየቅ ሄደው የነበር ቢሆንም ሀኪሞች አቤልን መጠየቅ እንደማይቻል ገልጸው መልሰዋቸዋል፡፡ 
አቤል ኤፍሬም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትና ማንንም ማናገር እንደማይችል ሆስፒታሉ ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች መረጃ ማግኘታቸውን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አቤል ኤፍሬም ማዕከላዊ ውስጥ በደረሰበት ድብደባ ኩሊላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ዛሬ ጠዋት 11 ሰዓት ጀምሮ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል እንደተወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments: