Tuesday, May 12, 2015

ፖሊስ የሰማያዊ አባላትን ማሰሩን ቀጥሏል


መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማሳሳት›› ጠርጥሬያቸዋልሁ ያላቸውን የሰማያዊ አባላት አሁንም ድረስ እያደነ ማሰሩን ቀጥሏል፡፡
ፖሊስ ዛሬ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነውን ናትናኤል ያለምዘውድ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ማሰሩ ታውቋል፡፡ 
መንግስት ቀደም ብሎ ያሰራቸው የፓርቲው አባላት ላይ ክስ በመመስረት ዋስትና ከልክሎ አስሮ የሚገኝ ሲሆን፣ በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ ደግሞ የስድስት ወር እስር መበየኑ ይታወሳል፡፡

No comments: