ስለዲሞክራሲ ብዙ ሲነግረን የኖረው የኢህአዴግ መንግስት የሚናገርለት ዲሞክራሲ በተግባር የሚታይ ዲሞክራሲ እንዲሆን ህዝብ ሲያደርግ ለቆየው ትግል ምላሹ አፈና ድብደባ እስርና ግድያ ሆኖ ቆይቷል፡፡
የህዝቡ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት በአሁኑ ሰዓትም የወያኔ መንግስት ምንም አይነት የባህሪ ለውጥ ሳያሳይ የዲሞክራሲ አፈናው ቀጥሏል፡፡
አሁን አሁንማ እነዚሁ የወያኔ መንግስት በአገሪቱ የሰላማዊ ሰልፎች እንዲሁም የተለያዩ የመብት ጥያቄዎች በምንም አይነት መልኩ እንዳይደረግ እያገዱ የህዝባችንን መብት እየነፈጉ ይገኛሉ ፡፡
ከዚህም አልፎ የተለያዩ ብሄሮችን በመከፋፈል ህዝቡ እርስ በእርሱ ተጋጭቶ የራሳቸውን ሰላም ለማስፈን እሩጫቸውን አጠናክረው ተያይዘውታል የኢትዮጵያ ህዝብ መኖር የሚፈልገው በሰላምና በህግ እንጂ በጉልበት እንዳልሆነ ሊገናዘበው ይገባል በድጋሚ በህግ በፍቅር እንጂ በጉልበት አንገዛም፡፡
No comments:
Post a Comment