Monday, May 11, 2015

የአንዳርጋቸው ፎቶ ...



ፎቶው አዲስ አይደለም። ፎቶው ላይ የተጻፈው ቀን Type የተደረገ ጽሁፍ እንጂ የእውነተኛ የካሜራ Font አይደለም። ባለ ድህረ ገጹ የወያኔ አገልጋዩ ቢንያም ከበደ የድህረ ገጹን www. የጻፈበት ሰማያዊ ቀለምና .com የጻፈበት ሰማያዊ ቀለም ልዩነት ያሳያል። www የጻፈበትና ቀኑ የተጻፈበት ሰማያዊ ቀለም አንድ አይነት ነው። ስለዚህ ቢንያም ከበደ ራሱ የጻፈው ቀን እንጂ ፎቶው የቆየ ነው። ማንኛውም ዲጂታል ካሜራ ቀናትን ቁጥርና በፊደል አደባልቆ 11th, 12th ይባስ ብሎ (ኮማ) ጨምሮ በጭራሽ አይጽፍም። ትክክለኛ ፎቶው የተነሳበት ቀን ቢሆን ኖሮ 11.05.2015 ይሆን ነበረ።

የአካባቢው ሁኔታ: - ምንም መኪና በአካባቢው አለመኖሩ ፎቶው የተነሳው መንገዱ አልቆ ለአገልግሎት ከመዋሉ በፊት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ። መንገዱ ለህዝብ አገልግሎት የዋለው 5 May 2014 ነበር። ስለዚህ ይህ ፎቶ ክዚህ ጊዜ በፊት የተነሳው ነው ብዬ እገምታለው። በሌላ አነጋገር ይህ ፎቶ አንድ አመት አልፎታል ማለት ነው።

ብዙ ጊዜ በጣም ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞች በዱላ ተደብድበው የሚታይ ቁስል እንዲኖርባቸው አይፈለግም። ስለዚህ እንደ አንዳርጋቸው አይነት እስረኞች ላይ ሊፈጸሙ ከሚችሉት ሶስት ዋና የሚባሉት ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ የኤሌክትሪክ እሳትን መጠቀም፣ ሰውነትን በማንጠልጠል፣ በመስቀል ወይም በመወጠር ማሰቃየት (Rack torture)፣ ሰዶማዊ ወይም የመደፈር ጥቃቶች ናቸው። እነዚህ አይነት ጥቃቶች አንድ የስፖርት ቱታ የለበሰ ሰው ላይ አይትዩም።

እኔ እንደማየው ይህ የአንዳርጋቸው ፎቶ ወያኔን የተቀላቀለ ወይም ያደነቀ ለማስመሰል የመንገድ ስራዎች የሚያደንቅ እዲመስል ያነሱት ፎቶ ከመሆኑ ሌላ ስለ ጤንነቱም ጭምር ብዙ ይነግረና። የእግሮቹ አቋቋም ላይ ለሚያተኩር ሰው አንዳርጋቸው መራመድ እንደሚችል ጥርጣሬ ውስጥ ይከተናል። ነገር ግን ከሁሉ በቅድሚያ የሚታየው ክብደት መቀነሱ ሲሆን ይህ ደግሞ ከውስጥ ህመም ወይም ከአመጋገብ ጋር የተያያዘ ችግር ሊኖርበት እንደሚችል ያሳያል ወይም ጥያቄ ያስነሳል። ሌላው የነጠላ ጫማው ጉዳይ ነው። እንደተለመደው የውስጥ እግራቸውን የሚገረፉ እስረኞች ቁስሉ እስከሚደርቅላቸው ለብዙ ሳምንታት በነጠላ ጫማ እንዲሄዱ ይደረጋሉ። እኔ የሚመስለኝ ነጠላ ጫማው ከውስጥ እግር ድብደባ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ነው። የፎቶው አነሳስ በግልጽ እንደሚያሳየው በተለይ እጆቹ ላይ ካተኮራችሁ ፎቶውን በሚነሳበት ወቅት ትዕዛዝ እየተቀበለ መሆኑን የሚያሳይ እንቅስቃሴ (body language) እንዳለው ግልጽ ነው። ፎቶ ለመነሳት ብቻ ከመኪና እንዲወርድ ከተደረገ በኋላ ወዲያውኑ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አፍነው የሚወስዱት እንጂ እንደተባለው ልማቱን ለማድነቅ ከእስር ቤት ያወጡት አይመስልም።

ከላይ እንዳልኩት ይህንን ፎቶ በተነሳበት ጊዜ ከአመት በፊት ሰውነቱ እንዲህ ከነበረ ዛሬ እንዴት ሊሆን እንደሚችል እናስብ። የሆነው ሆኖ ከዚህ በኋላ አንዳርጋቸው ቢፈታም ጤነኛ ሆኖ ወደነበረበት ትግል ይመለሳል ብሎ ማሰብ ከባድ ይመስለኛል። ረጅም እድሜ እንዳይኖረው አድርገው ይለቁታል እንጂ በድጋሚ ከሃገር ወጥቶ በመገናኛ ብዙሃን እንዲሰድባቸው የሚፈቅዱለት አይመስለኝም። ጭካኔያቸውንና ሰዶማዊ ባህሪያቸውን ስለምናውቅ የሚያረጉትን አድርገውት እንደ ብርቱካ ሚደቅሳ ዝም ያደጉታል። ይለቁታል።
ልጅ ግሩም

No comments: