Saturday, May 9, 2015

ወያኔ ሕዝብን አዘናግቶ በህዝብ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሞራል ድቀት የሚያስክትል ተጨማሪ ወንጀሎችን ሊሰራ አቅዷል

tplf1-620x310
ወያኔ ሕዝብን አዘናግቶ በህዝብ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሞራል ድቀት የሚያስክትል ተጨማሪ ወንጀሎችን ሊሰራ ስላቀደ በአስቸኳይ በአንድነት ተቀናጅተን ይህንን እኩይ ስርአት ልናስወግድ ይገባል::ከመቼውም ጊዜ በላይ እርስ በርስ መግባባትና መስማማት ያለብን አስቸኳይ ሰዓት ላይ ነን፡፡ምርጫውን ተከትሎ የሚወለደው ሕዝባዊ አመጽ ያስደነገጠው ወያኔ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን እና ጋዜጠኞችን የመፍታት እቅድ አለ የሚል ወያኔያዊ ፕሮፓጋንዳ ለማዘናጊያ/ለስልጣን ማስረዘሚያ እየረጨ ይገኛል:: ወያኔ ያልገባ ነገር ቢኖር ሕዝቡ የሚያደርገው ትግል ለለውጥ እንጂ እስረኞች ሲፈቱ ተሰብስቦ ሊቀመጥ አይደለም:;እስረኞቹ ራሳቸው የታሰሩት ለሕዝቦች ነጻነት እና መብት ሲታገሉ መሆኑን ማናችንም የምናውቀው ወያኔንም ሆዱን የቆረጠው ይህ መሆኑ እሙን ነው::

መንግስት ከሕዝብ ሳይግባባ ሲቀር ሕዝብ ከሕዝብ ጋር እንዳይግባባ የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም::በሃይማኖት በዘር በአስተሳሰብ ወዘተ እክይ ስራዎችን ተግቶ በመስራት ጥላቻን መዝራት የአምባገነኖች አንዱ ባህሪ ነው::ይህ ባህሪ በ አሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለማንቀሳቀስ ቢፈለግም ያለው ጨቋኝ ስርአት አልተሳካለትም::ሕዝብን እያባሉ በማደናገሪያ አሉባልታ እየረጩ እያረጋጉ እያዘናጉ አፍዝዞ መግደል..ይህ ወያኔያዊ ስልት ተነቅቷል::የተነቃበት ወያኔያዊ ስልት በመሆኑ ሕዝቡ በፍጹም በነጻነቱ እና በመብቱ ላይ እንደማይደራደር በተግባር የሚያስመሰክርበት ጊዜያት ቀርበዋል::የህዝብ የትግል ውጤት በግፍ የታሰሩ ንጹሃንን ነጻ ያወጣል:: በግፍ የተሰደዱትን ወደ ሃገር ቤት ይመልሳል::ፍትህ ላጡት ብርሃን ይሆናል::የህዝብ የትግል ውጤት…..

ያለንበት ሰዓት ላወቀው ይሁን ላላወቀው በእርስ በእርስ መግባባት እና መስማማት ላይ ተመስርተን በመቻቻል በአንድነት የምንቆምበት ሰአት ነው::ለወያኔ የማደናበሪያ እና የማዘናጊያ ስልቶች ሳንታለል ለነጻነት እና ለመብት የምናደርገውን ትግል በመሃል አገር ይሁን በዳር አገር ላይ ጠንክረን ልንገፋበት ግድ የሚለን አስረአንደኛው ሰአት ላይ መድረሳችንን ልንረዳ ይገባል::
ፍትህን አጥተው የሚገላቱ የሃይማኖት አባቶች እና ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች በጅምላ ታፍሰው ብየማጎሪያ ካምፑ የተከማቹ ወገኖቻችን ሁሉ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ያሉበት እቅት ላይ መሆናችንን ማወቅ ሲገባን ለኛ ነጻነት እና መብት መከበር ትግሉን ጀምረው የተሰዉ ኢትዮጵያውያንም ደም እየጮኽ ነው::ፍትህ አጥተው በየእስር ቤቱ የሚገላቱ ወገኖቻችን ቀጠሮ መርዘሙ በራሱ ከካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሳኔ አለመሰጠቱ በራሱ ሊያሳየን የሚችለው ነገር ቢኖር ምርጫውን በጁ ካደረገ በኋላ ወያኔ አዘናግቶና ተረጋግቶ በህዝብ ልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ድቀት ሊያስከትል የሚችል ተጨማሪ ወንጀል ለመስራት ማቀዱን ስለሆነ ጠንክረን በመታገል ይህንን ስር አት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልናሰወግድ ይገባል::

No comments: