Sunday, May 10, 2015

እነሆኝ እኛም ስናጣራ ቶሎ እንደ ማታጣሩ ተሰምቶናል – ከመኳንንት ታዬ(ፀሃፊ)

cherkos addis ababa
ሰሞኑ አንዳች ነገር በውስጤ ሲብላላ ነበርና በዚህ ይሁን ብሎ አውጥቶ ከቀለም ጋር ለማገኛኘት የደረሰብን ሃዘን እረፍት አልሰጥ ስላለኝ ቀን እንድወስድ ግድ ሆነ።ይሁንና ወገኖቻችን የሰውነት አግባብ በሌላቸው እራሳቸውን እንኳን በማይወክሉ ቡዱኖች እጅ ወደቁብን ።እርግጥ ነው ለኢትዮጲያ ክርስቲያን ሲደገስለት የኖረ ከሃገር ውስጥም ከውጭም ሁሌ የሚነገርው ነበር ።እንደ ከባድ ወንጀልም በክርስቲያንነቱ ቅጣቱን መቀበል እንዳለበት ብዙዎች ብዙ ብለዋል ።ለአሁን ለመፃፍ ያነሳሳኝ ይህ አልነበረም ።ይልቅስ ከባድ ግርምት ያደረብኝ መንግስታችን ከገዳዮቹ በላይ ምስክር ፈልጎ አላጣራንም እናጣራለን የሚሉ የሚኮሶኩሱ ቃላቶቹ ናቸው ። እነኚ ሰዎች እስከ መቼ ያጣራሉ? የሚል ትልቅ ጥያቄ ፈጠረብኝ ።እርግጥ ነው ከጅምሩ ስትገቡ ጀምሮ አስካሁን ብዙ ማጣራት ኖሮባችሁ ያላጣራችሁት ነገር ነበር ።ግን የምትኖሩት ከህዝቡ ተከልላችሁ በብረት አጥር ውስጥ ስለሆነ ኢትዮጲያዊ መልኩን ነብር ጅንጉርጉርነቱን አለም ያውቀዋል ያጣራዋል ግና ለእናንተ ይከብድ ይሆናል።ይሁን እንዲህ አይነቱ ስርአት በአፍሪካ የተለመደ ነው ። የእናተ በዛ ለማለት ያህል ነው እንጂ።
እሰቲ ለአብነት ያህል ማጣራት ኖሮባችሁ ሳታጣሩ እስከ ዛሬ በስልጣን ላይ እንዳለችሁ ጥቂት እንበል።ከጅምሩ ወደ ኢትዮጲያ ስትገቡ ባንዲራን ጨርቅ ነው በማለት ጀመራችሁ። እርግጥ ነው ወርቅ ነው አላልንም ግን ስንት ትውልድ እንደተገበረበት አላጣራችሁም ለማለት እንጂ።ቀጥላችሁ ኤርትራን ጨምሮ የአሰብ ወደብን ስታስወስዱ ኢትዮጲያ ያለ ባህር በር ስታስቀሯት ብሎም ትውልድ ጥያቄ ሊኖረው እናንተም ልተጠየቁ እንደምትችሉ አላጣራችሁም።ይኼም ብቻ አደለም ሃገሪቷን በሰላም ማስተዳደር ሲቻል በጎጥ በመንደር ከፋፍላችሁ ህዝብን ከህዝብ ስታጋጩ በመጨረሻው ችግር ሊያመጣ እንደሚችል አላጣራችሁም።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድ ዘር የበላይነትን አስፋፍታችሁ አየሩንና ንፋሱን ስትቆጣጠሩ አብሮ ተዋዶ በሚኖረው ህዝብ ከፍተኛ ክፈተት እንዲኖር ስታደርጉ እና እድገት ማለት የአንድ ዘር የበላይነት ሲመስላችሁ ህዝቡ በጥላቻ እንደሚመረዝ እና ብድር ከፋይ ልትሆኑ እንደምትችሉ አላጣራችሁም።ዛሬ የደረስንበት ደረጃ ከመድረሳችን በፊት ብዙ ያላጣራችሁት ነገር በማድረጋችሁ ዛሬ ላይ ደረስን።ስለ አክራሪነት እየሰባካችሁ ነገር ግን አክራሪዎች ከ አልሲሲ በፊት ቤተክርቲያን ሲያቃጥሉ ፤ሲያፈርሱ ክርስቲያኖችን በተለያየ ቦታ ሲገሉ ብሎም በባሌ በጅማና በሌሎች አካባቢዎች ክርስቲያኑ የቢለሃ እራት እየሆነ ባለበት ግዜ ሁሉ ይህ ነገር ፈር እየለቀቀ መንገድ እንደቀየረ አላጣራችሁም። ኢትዮጲያ ውስጥ እስላምና ክርስቲያን አብሮ መኖር የጀመረው ዛሬ አደለም ጥንት ነው ።
ይህ በሰላም አብሮ መኖር የለመደ ህዝብ ክፍተት ያመጣው አሁን በእናንተ ግዜ ነው ለዚህም ተጠያቂ ልትሆኑ እንደምትችሉ አላጣራችሁም። ብሎም ክርስቲያኑን አንዴ ገዳሙን ስታፈርሱበት፤ አንዴ ምነኩሳቱን እያሳደዳችሁ ቤተክርስቲያኑን ስታፈርሱ ፤ታሪክ ጠገብ ገዳማትን ደብዛቸውን ስታጠፉ፤አልፎ ተርፎ የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ማሕተቡን እንደምታስበጥሱት ስታወጁ ብሎም አጠፋነው ስትሉ እና ክርስቲያኑ ህዝብ ሲታገሳችሁ ይህን ያያችሁትን ያህል ሃይል እንዳለውና መታገስ እንጂ መቀለድ እንዳማያቅ እስከሞትም የታመነ እንደሆነ አላጣራችሁም። በሰላም ቤቱ የሚኖረውን በልማት ስም እያፈናቀላችሁ መኖሪያ ስታሳጡት ብሎም በብሔሩ ምክንያት ሰርቶ እንዳይኖር እያስመረራችሁት መፍትሔ ሲያጣ ይህም አልበቃ ብሎ አራጣ አበዳሪው አንድ መንግስት ሆኖ ደሃውን በብድር ስም የኖረበትን ሲያስለቅቀው ፤ አገር ማለት ለነዋሪው የስቃይ መንደር ከሆነች የተወለደበት ሃገር አለቃና ምንዝሩን መለየት አስቸግሮ ማንም የፖለቲካ ተሿሚ እስከሆነ ድረስና በስልጣን እስካለ ድረስ የፈለውገውን የሚያደርግበት ስርአት ባለበት ሁኔታ ላይ ከመሬት ብሆን ጅቡ መካራ ከዛፍ ብወጣ ነብሩ መከራ ብሎ ለቆ እየወጣ በባሕር እየገባ ሲሞት የአሳ እራት ሲሆን ካተረፋችሁት የከሰራችሁት እንደሚበዛ አላጣራችሁም ። አስኪ ልብ በሉ አጣሩ፤ ስንት ሚሊዮን በር አካብታችኋል? እያንዳንዳችሁ ስንት ህንፃ አላችሁ?ኢትዮጲያ ስንት ቢሊዮን ዶላር እዳ አለባት ?እናንተ በውጭ ሃገር ስንት ቢሊዮን ዶላር አካብታችኋል? ይህ ከሆነ ደሃው ምን ሊደርሰው ሞቱን ቁጭ ብሎ ይጠብቅ?ሌላ ቢቀር የሚበላውን እንኳ ባለው ገንዘብ እንዳይገዛ ካለችሁ ከእናንተ ጋር ሆነ ወድድሩ።

በዚህ ምክንያት ሃገሩን ለቆ እንደሚወጣ አላጣራችሁም ። ብሎም ዛሬ በቢለሃ ሲታረድ የ አረደው ክፍል ወገኖቻችሁን ገደልኩ እያለ እንተ ግን ከመደንገጥ ይልቅ ሳታፍሩ በአደባባይ ወጥታችሁ አላጣራንም ስትሉ ከባድ ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል አላጣራችሁም ።ዛሬ የሚነገረው ለደላላ ብዙ ብር ከፍሎ ከሃገር ለምን ይወጣል ?ይባላል። ነገር ግን ባለው ብር ሐገሩ ላይ እንዳይሰራ ልቅ የወጣው ሙስና ፤ስግብግብነት፤የፖለቲካ አባል ካልሆነ እንኳን መስራት መማር እንኳን ጥያቄ ውስጥ ባለበት ባሁኑ ግዜ ይህን እንዳማራጭ ቢወሰወድ ለጥፋቱም የእናንተ ከአቅም በታች የሆነ አስተዳደር እንደሆነ አላጣራችሁም። በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታችሁ አንድ አንዳርጋቸውን ያዝን ብላችሁ ስትፈነድቁ ከውስጥም ከውጭም የሚያሳጣችሁ ነገር እንዳለ አላጠራችሁም ።በተቆጣጠራችሁት የዜና ማሰራጫ እንኳን ሳይቀር ሁሌ ተስፋ አስቆራጭ እና ያልተጨበጠ ወሬ ስለምታወሩ ከህዝቡ ጋር ልብ ለልብ ያላችሁ ቀረቤታ እርቋል። ዝም ብሎ የሚሰማችሁ እንጂ የሚያምናችሁ አላፈራችሁም ። በ97 ዓ.ም ትላንት ለሆዳችን ዛሬ ለሃገራችን ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ያላችሁበትን ቦታ አላጣራችሁም። የሚበላውን እህል ገበሬው ድረስ በመሄድ እየሸመታችሁ ስታስወድዱበት እና እጅ እንዲያጥረው ስታደርጉት “የሚበላውን ያጣ ትውልድ መሪውን ይበላል” የሚለውን አባባል ሊፈፀም እንደሚችል አላጣራችሁም ።
ከባህሉ ጋር የማይመጥን ነገር ብዙ ነገር አስተማራችሁት ።ግብረ ሰዶማዊነት ሌላው ትልቅ በሽታ እየሆ እንደሆነ እና የከፋ ነገር እየመጣ እንደ ሆነ አላጣራችሁም ። ነገር ግን ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን ህዝብ ለመወንጀል የኮምንኬሽን ጉዳይ ሚ/ሩ የሰልፈኛውን እግር አነሳስ አሰላለፍ አጣርቶ ተጠንቶበት እንደሆነ ማጣራቱን ሲገለፅ ነበር።ያ ማለት ክርስቲያኖች ሲታረዱ ሰማያዊ ፓርቲ አለበት ማለት ነው፤ የሚል ትርጓሜ ያሰጠዋል። ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ወንበዴ ቡድን ጋር መኖሩን አጣርተናል ካላችሁ እንዴት የገዛ ዜጎቻችሁን በማየት ማጣራት ሳትችሉ ገዳዩ ቡድን ኢትዮጲያዊ ናቸው ሲል አላጣራችሁም?። በየእስር ቤቱ ብዙ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች በአሸባሪ ስም ሲታሰሩ አለም የለም የወሰዳችሁት እርምጃ ልክ አደለም ሲል እናንተ ለገዛ ወንድሞቻችሁ አሸባሪ የሚለውን ስም ስትሰጡ አለም አሸበሪ ካላቸው ጋር ያለውን ልዩነት አላጣራችሁም።ዛሬም ከዚ ሁሉ በኋላ የስህተት መንገዱን አጣርታችሁ ለመዝጋት ሳይሆን ሳታጠሩ የገዛ ህዝባችሁን በየእስር ቤት በማጎርና በማሰቃየት ላይ ተጠምዳችኋል። ይህን ሁሉ ስል አልሰራችሁም ለማለት አደለም ።የሰራችሁትን አመሰግናለሁ።ግን አቅም ቢኖራችሁ 100 አመትም በተቀመጣችሁ። ነገር ግን ኢትዮጲያን ገና አላጣራችኋትም ለዚህ ብዙ ነገር ጠፋ ።
ethiopians isis
ለዚህ ነው እናንተ እስክታጣሩ ድረስ አስቀድሞ ያጣራት ደግሞ ተራ ይድረሰው። በዛውም ልጆቻችሁም እናንተም በሰላም እየኖራችሁ እስቲ ደግሞ ሃገራችሁን ባህሏን ህዝቧን ብቻ ሁሉንም አስክታጣሩ ቆም ብሎ ለማየት እድል ታገኛላችሁ።ከቂም ከበቀል የፀዳ ትውልድ ይፈጠር ።ግድለም የኢትዮጲያ ህዝብ ቂመኛ አደለም ።ነፃ ሆናችሁ ለመኖር እድሉን አይነፍጋችሁም ።ብሔራዊ እርቅ ላይ አተኩሩ።ነገን አስቡ። በግድ የያዙት በግድ ሲለቁት አንዳች ነገር በጭቆ መነሳቱ አይቀሬ ነው ።ይህ ደግሞ እኔም ይህን ፅሁፍ የፃፍኩትን ሆነ ሌሎቹን እናንተን ጨምሮ የምንወደው አይመስለኝም ።ለማጣራትም ከእንቅልፍ መንቃት የማይሸምቱት ብልጠት መሆኑን የምታቁበት ግዜው ዛሬ ነውና።እነሆኝ እኛም ስናጣራ ቶሎ እንደ ማታጣሩ ተሰምቶናልና አረፍ ማለታችሁን ሽተናል። ለዚህ ግዜው አሁን ስለሆነ፤ ለሆነው ሁሉ ለምን አላጣራችሁም እንደማንል ይኸው በኔ በኩል ቃሌን አስዤአለሁ።
ቸር ወሬ ያሰማን
Source: Zehabesha

No comments: